1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔራዊ ፓርቲ ምሥረታ ጉባኤ

ሐሙስ፣ ግንቦት 1 2011

ዜግነትን እና ማኅበራዊ ፍትሕን መሠረት ያደረገ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ መሥራች ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ። ስድስት ኪሎ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በተከፈተው ስብሰባ ላይ ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ከተለያዩ ወረዳዎች የተወከሉ አባላት እንደተሳተፉ የጉባኤው አዘጋጆች ለዶይቼ ቬለ DW ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3IEyA
Oppositionsparteien Äthiopien
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ጉባኤው ነገ የአመራር አካላቱን እንደሚመርጥ ይጠበቃል

 ጉባኤው በዛሬው ዕለት ሕገ ደንቡን የሚያጸድቅ ሲሆን በነገው ዕለት ደግሞ የፓርቲው አርማ እና የአመራር አባላት ምርጫ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባኤው አርበኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ ራሳቸውን ያከሰሙ ሰባት ፓርቲዎች የተሰባሰቡበት ነው። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ አጭር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ