1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታኒያ ፍቺ እና የአነስተኛ የንግድ ሥራ ፈተና 

ቅዳሜ፣ የካቲት 30 2011

ብሪታኒያ በመጪው መጋቢት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአውሮጳ ኅብረት አባልነቷ ትወጣለች ተብሎ ይጠበቃል። የብሪታኒያ ፖለቲከኞች አገራቸው በምን አይነት ሥምምነት ከኅብረቱ ትውጣ በሚለው ጉዳይ ላይ እስካሁን ከስምምነት አልደረሱም።

https://p.dw.com/p/3Eiwu
England, London: Brexit Proteste
ምስል Reuters/H. Nicholls

የብሪታኒያ መንግሥት ውሳኔውን እንደገና ያጢን የሚሉ አልጠፉም

ብሪታኒያ በመጪው መጋቢት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአውሮጳ ኅብረት አባልነቷ ትወጣለች ተብሎ ይጠበቃል። የብሪታኒያ ፖለቲከኞች አገራቸው በምን አይነት ሥምምነት ከኅብረቱ ትውጣ በሚለው ጉዳይ ላይ እስካሁን ከስምምነት አልደረሱም። ብሪታኒያ ከአውሮጳ ኅብረት የምትወጣበት ጊዜ እየተቃረበ በመጣ ቁጥር ውሳኔው በአገሪቱ ምጣኔ-ሐብት ላይ የሚያሳድረው ጫና በርካቶችን ያሳስብ ይዟል። አነስተኛ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ከ1200 በላይ  የለንደን ነዋሪዎች የጠቅላይ ምኒስትር ቴሬሳ ሜይ መንግሥት ጉዳዩን እንደገና ለሕዝብ እንዲያቀርብ በፊርማ ጠይቀዋል። የለንደኗ ሐና ደምሴ በጉዳዩ ላይ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች። 
ሐና ደምሴ 
እሸቴ በቀለ