1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ አዲስ መንግሥት

ረቡዕ፣ ግንቦት 4 2002

በምርጫዉ ከፍተኛዉን መቀመጫ ያገኘዉ ወግአጥባቂዉ ፓርቲ ሰወስተኛዉን ከፍተኛ ድምፅ ካገኘዉ ከነፃ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጋር ተጣማሪ መንግሥት ለመመስረት ተገደዋል

https://p.dw.com/p/NMPe
ካሜሩንምስል AP

ብሪታንያ እስከ ትናንት የመሯትን ጠቅላይ ሚንስትር ጎርደን ብራዉንን ከነ ፓርቲያቸዉ ከስልጣን አሠናብታ የወግ አጥባቂዉን ፓርቲ በመንግሥትነት፥ መሪዉን ዴቬድ ካሜሩንን ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትርነት መርጣለች።ባለፈዉ ሐሙስ በተደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ ከተፎካከሩት ፓርቲዎች መካከል ብቻዉን መንግሥት መመሥረት የሚያስችል ድምፅ ያገኘ ፓርቲ የለም።በዚሕም ምክንያት በምርጫዉ ከፍተኛዉን መቀመጫ ያገኘዉ ወግአጥባቂዉ ፓርቲ ሰወስተኛዉን ከፍተኛ ድምፅ ካገኘዉ ከነፃ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጋር ተጣማሪ መንግሥት ለመመስረት ተገደዋል።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ