1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሬግዚት ውል ዳግም ውድቅ ተደረገ

ረቡዕ፣ መጋቢት 4 2011

ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ከአውሮጳ ሕብረት ጋር የተስማሙበትን ሀገራቸው ከሕብረቱ የምትወጣበትን ውል ለሁለተኛ ጊዜ ትንናት ማታ ውድቅ አድርጎታል። ፓርላማው በተለይ ብሪታንያ ከሕብረቱ አባልነት ከለቀቀች በኋላ በሰሜን አየርላንድ እና በአየርላንድ መካከል ያለው ድንበር ክፍት ሆኖ እንዲቆይ የሚጠይቀውን የውሉን ክፍል ነው የተቃወመው።

https://p.dw.com/p/3Ey3F
UK Brexit l Britische und Europäische Flagge
ምስል Reuters/E. Keogh

የብሬግዚት ውል ዳግም ውድቅ ተደረገ

 
የብሪታንያ ፓርላማ ብሪታንያ ከ16 ቀናት በኋላ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ያለ ስምምነት መውጣት አለመውጣቷ ላይ ዛሬ ማምሻውን ድምጽ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ፓርላማው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ከአውሮጳ ህብረት ጋር የተስማሙበትን ሀገራቸው ከህብረቱ የምትወጣበትን ውል ለሁለተኛ ጊዜ ትንናት ማታ በሰጠው ድምጽ ውድቅ አድርጎታል። ፓርላማው በተለይ ብሪታንያ ከህብረቱ አባልነት ከለቀቀች በኋላ በሰሜን አየርላንድ እና በአየርላንድ መካከል ያለው ድንበር ክፍት ሆኖ እንዲቆይ የሚጠይቀውን የውሉን ክፍል ነው የተቃወመው። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ተጨማሪ ዘገባ አዘጋጅቷል።
ገበያው ንጉሤ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ