1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪክስ ጉባኤ

ሰኞ፣ መጋቢት 16 2005

የብሪክስ አባል አገራት መሪዎች ነገ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በሚያደርጉት ጉባኤ እንደ አዲስ የጋራ ስምምነት መፈለጉን ቀጥለዋል።የብሪክስ (BRICS) ቡድን የአምስቱ ሀገራት ማለትም የ ብራዚል፣ሩሲያ፣ ህንድ ፣ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃ ስብስብ ነው።

https://p.dw.com/p/183ga
BRICS Logo vom kommenden Gipfel in Durban Südafrika März 2013

ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የሚያሳዩ እነኚህ የ ሶስት ቢሊዮን ህዝብ ሀገራት ፍላጎት የአውሮፓ እና የዮናይትድ እስቴትስን ግዙፍ ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚፈልጉ ናቸው።

--- DW-Grafik: Peter Steinmetz Redakteurin: Maja Braun
የብሪክስ ሀገራት


ብሪክስ ወደፊት ግብፅን ጨምሮ ኢ-ብሪክስ ይባል ይሆን? አባል ሀገራቱ ራሳቸውን ገና በሚፈልጉበት በዚሁ ወቅት የግብፁ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ሀገራቸው ብሪክስ ቡድንን ለመቀላቀል እንደምትፈልግ ጉባኤው ሲደርስ አሳውቀዋል። ጉባኤው በደርብን - ደቡብ አፍሪቃ ነው የሚካሄደው።
ቤርትልስማን የተባለው የጀርመን ተቋም ጥናት እንደሚያሳየው በጉባኤው ሁሉም ጉዳዮች መነሳታቸው አይቀርም። ዋናዎቹ ግን ሁለት ናቸው። አዝጋሚው የፖለቲካ ተሀድሶ ለውጥ እና በጣም አስቸኳዩ የማህበራዊ ፍትህ እጦት። የቤርትልስማን ተመራማሪ ናጂም አዛሀፍ፤ «በተናጥል እያንዳንዱን ሀገራት ስንመለከት በጋራ የሚጋሩት የማህበራዊ ፍትህ እጦቱን ነው።እንደሚመስለኝ የጋሪዮሻቸው ቢታወቅ እና የምጣኔ ሀብቱ እድገት ከማህበራዊ ብልፅግናው ጋ ቢዋሃድ የመጀመሪያው ርምጃ ይሆናል። ያኔ የብሪክስ ሃገራት አንድ ርምጃ ወደፊት ይራመዳሉ።»

በተለይ በመጨረሻ ቡድኑን የተቀላቀለችው ሀገርና ጉባኤው የሚካሄድባት ደቡብ አፍሪቃ ይህን በተመለከተ ጥሩ ነጥብ አልነበራትም። « እነኚህ አንድ አላማ ያላቸውን ሀገራት በቀጥታ ማመሳሰሉ ትንሽ ጥንቃቄን ይጠይቃል። ይሁንና በተለይ ደቡብ አፍሪቃ እንደቀድሞው የማህበራዊ ችግሮችን እየተጋፈጠች መሆኑ ግልፅ ነው።»

(L-R) Brazil's President Dilma Rousseff, Russian President Dmitry Medvedev, India's Prime Minister Manmohan Singh, Chinese President Hu Jintao and South Africa's President Jacob Zuma pose for a photograph during the BRICS summit in New Delhi March 29, 2012. REUTERS/Yekaterina Shtukina/RIA Novosti/Kremlin (INDIA - Tags: POLITICS) THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
እኢአ መጋቢት 1012 በኒው ዴሊ የተካሄደው የብሪክስ ጉባኤምስል Reuters


ስለሆነም አስተናጋጇ ሀገር በጉባኤው ላይ አንዳንድ ነጥቦች ማቅረብ ፈልጋለች። ከነዚህ ነጥቦች አንዱ ለረጅም ጊዜ ሲታቀድ የነበረው የደቡብ ደቡብ የልማት ባንክን መመስረት ነው። ለብሪክስ አባላት እና ለአዳጊ ሀገራት ብቻ የታሰበው ይሄው ባንክ የአለም ባንክ ተቋማት እና የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF ሻዶምስኪ እንደሚለው ተፎካካሪ እንዲሆን የታለመ ነው። ይህንንም ዕውን ለማድረግ የብሪክስ ሃገራት በባንኩ አማካኝነት የ50 ቢሊዮን ዮሮ የልማት እና የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት በተግባር ላይ ለማዋል አቅደዋል። የአለም ባንክ ይህንን ተቀብሏል። ይሁንና « ከባድ ኃላፊነት» እንደሆነ ሳይጠቅስ አላለፈም።
አዲሱ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ቺ ፒንግ በመጀመሪያው የውጭ ሀገር ጉብኝታቸው ፍላጎታቸው ግልፅ እንደነበር የብሪክስን አቋም የሚያጠኑት ቴተር ድራፐር ይገልፃሉ።
« ምጣኔ ሀብትን በተመለከተ ብሪክስ ማለት ቻይና እና የተቀሩት ሀገራት ማለት ነው። የሺ ቺ ፒንግ ጉብኝት እጅግ ወሳኝ እና ቻይና ብሪክስን ምን ያህል አትኩራ እንደምታይ የሚያንፀባርቅ ነበር። ቻይና የብሪክስ ቡድንን እንደ ጠቃሚ፣ ምናልባትም እንደ ጂ- ሰባት ሀገራት አማራጭ ቡድን ነው የምትመለከተው። ቻይና እንደ ሌላኛዋ አባል ሀገር ሳይሆን ለብሪክስ ህይወት መስጠት ትፈልጋለች። ይኼን ስል ሩሲያን ነው የማስበው። »


ይህ ብቻ አይደለም፤ ያሁኑ ጉባኤ ከበፊቶቹ ጋ ሲነፃፀር ይበልጥ ፖለቲካ የሚንፀባረቅበት ነው ይላሉ ፤ቴተር ድራፐር « ሌላው መመልከት የሚገባው ስለፀጥታው ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ ባለፈው ህንድ ከተካሄደው ጉባኤ ለየት ያደርገዋል። በተለይ ቀውስ በሚታይበት በመካከለኛው ምስራቅ የብሪክስ ሃገራት የጋራ አቋም ያላቸው ስለሚመስል፤ይህን በተመለከተ ማብራሪያ እጠብቃለሁ። ይህ ብቻ ሳይሆን የኢራን ፣ የሶሪያን እንዲሁም ምናልባትም አፍጋኒስታንንም በተመለከተ።»
በርግጥ ግብፅ የብሪክስ ሃገራትን ስለመቀላቀሏ ገና በግልፅ የተወሰደ ርምጃ የለም። ፕሬዚዳንት ሙርሲ ግን በደርበን ተገኝተው አዲስ ሙከራ ማድረጋቸው አይቀሬ ነው። ይሁንና በፖለቲካ እና በምጣኔ ሀብቷ የምትንገዳገደዋን ግብፅን የብሪክስ ሀገራት በአባልነት መቀበላቸው አጠራጣሪ ነው። ከግብፅ ይልቅ ሚስት በሚል ምህፃረ ቃል የሚጠሩት ሜክሲኮ፣ ቱርክ፣ ደቡብ ኮሪያ እና አንዶኔዢያ የበለጠ አባል የመሆን እድል አላቸው።


ሉድገር ሻዶምእስኪ
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ