1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብራስልስ የፀጥታ ሁኔታ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 20 2008

ባለፈው ማክሰኞ ብራስልስ አዉሮፕላን ማረፊያ እና አንድ የምድር ዉስጥ የባቡር ጣቢያ ላይ በደረሱት ሦስት የቦምብ ፍንዳታዎች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ31 ወደ 35 ከፍ ብሏል።

https://p.dw.com/p/1ILWf
Schaubild Terrornetzwerk Belgien anderer Ausschnitt
ምስል DW/B.Riegert

ዛቫቴም አዉሮፕላን ማረፊያ በደረሰው የሽብር ጥቃት እጁ እንዳለበት የተጠረጠው እና በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ሶስተኛው ሰውም በቂ ማስረጃ አልተገኘበትም በሚል ተለቋል። እንደ የብራስልስ ከንቲባ ከሆነ፣ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ፋይሳል ሼፉ መለቀቅ አልነበረበትም። ከንቲባው ምንም እንኳን ፋይሳል ሼፉ ከአይሮፕላን ማረፊያው ጥቃት ጋር በተያያዘ ተይዞ መቆየት ባይችልም፤ ግለሰቡ ከወንጀል ንጹህ እንዳልሆነ ዛሬ ለሀገራቸው የመገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል። ቤልጂየም አሁንም ተጠርጣሪዎችን እያሰሰች እና እየመረመረች ትገኛለች። ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የብራስልስ አዉሮፕላን ማረፊያም ስራ አልጀመረም።

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ