1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሬግዚት ቀነ ቀጠሮ ተራዘመ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2011

አዉሮጳ ኅብረት ልዩ ጉባዔ ብሪታንያ ከኅብረቱ የምትወጣበትን እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር የፊታችን ጥቅምት 31 ድረስ በድጋሚ እንዲወሰን ትናንት ባካሄደዉ ልዩ ጉባዔ ወሰነ። ኅብረቱ ከዚህ ቀደም ባካሄደዉ ጉባዔ እስከ ዛሬ 3 መጋቢት ሦስት ድረስ የመዉጫ ስምምነቱን ብሪታንያ ካላፀደቀች ነገ ያለምንም ስምምነት እንድትወጣ ተወስኖ ነበር።

https://p.dw.com/p/3Gcvg
Belgien Brüssel - Donald Tusk, Theresa May und Angela Merkel
ምስል picture-alliance/empics/L. Neal

ብሪታንያ ነገዉ ከኅብረቱ ያለምንንም ሥምምነት ልትወጣ ትችል ነበር

የአዉሮጳ ኅብረት ልዩ ጉባዔ ብሪታንያ ከኅብረቱ የምትወጣበትን እንደአዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር የፊታችን ጥቅምት 31 ድረስ በግጋሚ እንዲወሰን ትናንት ባካሄደዉ ልዩ ጉባዔ ወስኖአል። ኅብረቱ ባላፈዉ ባካሄደዉ የመሪዎች ጉባዔ እስከዛሬ ማለት መጋቢት ሦስት ድረስ የመዉጫ ስምምነቱን ብሪታንያ ካላፀደቀች ፤ በነገዉ እለት ከኅብረቱ ያለምንንም ሥምምነት እንድትወጣ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም አቅላይ ሚኒስትር ሜይ ግን ስምምነቱ በፓርላማቸዉ ባለማለፉ ሃገራቸዉ እንዲሁ ያለስምምነት እንዳትወጣ ለመከላከል ጊዜዉ ዳግም እንዲራዘም በጠየቁት መሰረት ነዉ ትናንት ኅብረቱ ባካሄደዉ ልዩ ጉባዔ የመዉጫዉ ቀን እንዲራዘም የተወሰነዉ ። የብረስልሱ ወኪላችን ተጨማሪ ዘገባ አለዉ። 

 

ገበያዉ ንጉሴ  

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ