1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 17 2004

ከአቡነ ጳውሎስ ግብዐተ መሬት በፊት በተካሄደው ፀሎተ ፍታት ላይ ከግሪክና ከግብፅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን የመጡ የሃይማኖት አባቶች ተካፍለዋል ። በሥነ ሥርአቱ ላይ የውጭ እንግዶች የመንግሥት ባለሥልጣናትና በርካታ የቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን ተገኝተዋል ።

https://p.dw.com/p/15vlv
Begräbnis des Patriarchen der äthiopisch-orthodoxen Kirche, Abune Paulos *** Autor/Copyright: Getachew Tedla/DW, 23.08.2012
ምስል DW

የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርአት ዛሬ ከሰዓት በኋላ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል ። ላለፉት 20 አመታት የቤተክርስቲያኗ ፓትሪያርክ ከነበሩት ከአቡነ ጳውሎስ ግብዐተ መሬት በፊት በተካሄደው ፀሎተ ፍታት ላይ ከግሪክና ከግብፅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን የመጡ የሃይማኖት አባቶች ተካፍለዋል ።በሥነ ስርአቱ ላይ የውጭ እንግዶች የመንግሥት ባለሥልጣናትና በርካታ የቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን መገኘታቸውን ጊታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል ። አቡነ ጳውሎስ ባደረባቸው ሕመም በ 76 ዓመት ዕደሜ ከዚህች ዓለም የተለዩት ባለፈው ሣምንት ነበር።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ