1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቦሩስያ ዶርትሙንድ የእግር ኳስ ቡድን አውቶቡስ ጥቃት ተጠረጣሪ መያዙ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 13 2009

የጀርመኑን ቦሩስያ ዶርትሙንድ የእግር ኳስ ቡድን አባላትን ይዞ ይጓዝ በነበረ አውቶቡስ ላይ ጥቃት ከተጣለ ከአንድ ሳምንት በኋላ ምርመራውን የሚያካሂደው ቡድን አንድ ተጠርጣሪ መያዙን የጀርመን  ፌዴራል አቃቤ ሕግ  አረጋገጠ። በ ፌደራል አቃቤ ሕጉ ገለጻ መሰረት፣ ተጠርጣሪው በቱቢንገን አካባቢ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

https://p.dw.com/p/2bewH
Deutschland Explosionen an BVB-Bus
ምስል picture-alliance/dpa/M. Kusch

የቦሩስያ ዶርትሙንድ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረው አውቶቡስ ላይ በፈንጂ ለተጣለው ጥቃት ተጠያቂ ተብሎ የታሰረው በመጠርጠር የታሰረው ግለሰብ  የ28 ዓመቱ ተጠርጣሪ የጀርመን እና የሩስያ ዜግነት እንዳለው ተገልጿል። የቦሩስያ ዶርትሙንድ ቡድን ተጫዋቾች ከፈረንሣዩ ሞናኮ ጋር ለነበረው የሻምፒዮንስ ሊግ ግጥማያ በአውቶቡስ ወደ ሜዳው በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር ፍንዳታው የደረሰው ። ከምሽቱ አንድ ሰአት ከሩብ ሲል ከተከረከመ የተክል አጥር ጥግ ላይ በደረሰው ሦስት ተከታታይ ፍንዳታ ተጨዋቾቹን ጭኖ የነበረው አውቶቡስ መስኮት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። እንዲያም ኾኖ   አንድ ተጨዋች ብቻ ከመስተዋት ስብርባሪ ፍንጣሪ እጁ ላይ ጉዳት ከመድረሱ ውጪ ሌሎች ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጧል።  ፈንጂው የብረት ቁጥርጥራጮች እንደነበሩበት ተገልጧል።

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ