1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቦይንግ 737 አደጋ አንደኛ ዓመት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2012

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን  ተከስክሶ የ157 መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች ሕይወት የተቀጠፈበት አደጋ ከደረሰ ዛሬ አንድ  ዓመት ደፈነ።

https://p.dw.com/p/3ZASG
Äthiopien Jahrestag Absturz Boeing 737 max 8
ምስል DW/S. Muchieu

«የኢትዮጵያ አየር መንገድ መታሰቢያ»

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን  ተከስክሶ የ157 መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች ሕይወት የተቀጠፈበት አደጋ ከደረሰ ዛሬ አንድ  ዓመት ደፈነ። የአደጋውን ሰለባዎች የሚያዘክሩ የተለያዩ ዝግጅቶች ከትናንት በስተያ እሁድ ጀምሮ በተለያዩ ስፍራዎች እየተካሄዱ ነው። ዛሬም በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦች አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ስፍራ በመገኘት ሙት ዓመቱን አስበዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩል በአብራሪዎች ክበብ ቅጥር ግቢ ውስጥ ማምሻውን የመታሰቢያ ሥርዓት እያካሄደ ነው። ዝግጅቱ  ይጀመራል ከተባለው ሰዓት ዘግይቶ ሊጀመር አካባቢ በስፍራው የሚገኘውን ዘጋቢያችንን ሰሎሞን ሙጬን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬዋለሁ።

ሰሎሞን ሙጬን

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ