1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቫሌታዉ ጉባኤ እና አፍሪቃ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 4 2008

በአስቸጋሪ የበረሃ እና የዉኃ ላይ ጉዞ አልፈዉ ወደአዉሮጳ ከሚገቡት መካከል አፍሪቃዉያን እንደሚበረክቱ ይነገራል።

https://p.dw.com/p/1H5up
EU Afrika Gipfel 2015
ምስል Getty Images/AFP/F. Monteforte

[No title]

ሳይጠበቅ ከየአቅጣጫዉ በመጡ በርካታ ስደተኞች የተጥለቀለቁት የአዉሮጳ ሃገራት በተለይ አብዛኞቹ የኤኮኖሚ ስደተኞች ናቸዉ የሚሏቸዉን የአፍሪቃዉያን ስደተኞች ፍሰት ቢቻል ለመግታት ካልሆነም ለመቀነስ ከአህጉሪቱ መሪዎች ጋር ለመነጋገር ጉባኤ አካሂደዋል። በማልታ ዋና ከተማ ቫሌታ ላይ ለሁለት ቀናት በተካሄደዉ የዉይይት መድረክ ላይም የአዉሮጳ ሃገራት መሪዎች በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የልማት ሥራዎችን ለማስፋፋትና የሥራ ዕድሎችን ለመክፈት እንዲቻል የ1,8 ቢሊየን ዩሮ ርዳታ ለመስጠትም ቃል ገብተዋል። ገንዘቡ እስካሁን ተሟልቶ ባይዘጋጅም ተንታኞች እና የመብት ተሟጋቾች ይህ ብቻዉን ስደትን ለመግታት መፍትሄ አይሆን በማለት ሳይተቹት አላለፉም።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ