1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድና የዓለም ባንክ ባለሥልጣናት የኢትዮጵያ ጉብኝት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 18 2007

የአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ሰላም እና ፀጥታን ለማጠናከር እንዲሰሩ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን እና የዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ጂም ዮንግ ጂም፣ እንዲሁም፣ በኢትዮጵያ የአውሮጳ ህብረት ተጠሪ ማርኮ ካማሮ ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/1DdKu
የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን እና የዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ጂም ዮንግ ጂም በአዲስ አበባምስል DW/G.T. Haile-Giorgis

ስምንቱ የአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ያካባቢያቸውን ፖለቲካዊ መረጋጋት ለማስፋፋት እና ኤኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስገኘት ለሚያደርጉት ጥረት መደገፊያም የተመድ፣ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪቃ የልማት ባንክ፣ የሙሥሊሞች የልማት ባንክ እና የአውሮጳ ህብረት በቀጣዮቹ ዓመታት ስምንት ቢልዮን ዶላር ርዳታ እንደሚሰጡ ከኢትዮጵያ ቀጥለው ኬንያን የሚጎበኙት ባለሥልጣናት ቃል ገብተዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ