1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድና የዓለም ፀጥታ ጉዳይ

ማክሰኞ፣ መስከረም 18 2008

በዓለም የሚታዩ ደም አፋሳሽ ውዝግቦችን ለማብቃት ወይም ለመቀነስ የሚደረገው ሰላም የማስከበር ጥረት ከጊዜ ወደጊዜ አዳጋች እየሆነ መሄዱ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1GfUS
Symbolbild UN Blauhelme
ምስል MENAHEM KAHANA/AFP/Getty Images

[No title]

እርግጥ፣ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮዎች ለውዝግቦች ሁሉ መፍትሔ ባያስገኝም፣ ጦርነቶችን እና ውጊያዎችን በመታገሉ ረገድ ሁነኛ መሳሪያዎች ሆነው እንደሚያገለግሉ ትናንት በተከፈተው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገልጾዋል።በዚሁ መሰረትም፣ በመላው ዓለም የሚካሄዱ የሰላም ማስከበሪያ ተልዕኮዎችን በተመለከተ ዩኤስ አሜሪካ ትናንት ከ160 የሚበልጡ ሃገራት መሪዎች ከተሳተፉበት የዘንድሮው ጉባዔ ጎን ለጎን አንድ ልዩ ስብሰባ ጠርታ ነበር፣ ስለስብሰባ ዓላማ እና ውጤቱ ፣ እንዲሁም፣ የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የዩኤስ አሜሪካ አቻቸው ባራክ ኦባማ ከአንድ ዓመት ከበለጠ ጊዜ በኋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ስላካሄዱት ውይይት ይዘት በዋሽንግተን የሚገኘውን ጋዜጠኛ በስልክ ጠይቀናል።

ናትናኤል ወልዴ / አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ