1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ የንግድና የልማት ጉባዔ በአክራ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 15 2000

የተመድ የንግድና የልማት ጉባዔ በምህጻሩ ኡንክታድ ካለፈው እሁድ ወዲህ ጋና መዲና አክራ ላይ አስራ ሁለተኛውን ዓቢይ ጉባዔ በማካሄድ ላይ ይገኛል። አምስት ቀናት የሚቆየው ይኸው ጉባዔ በአንድ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገር ሲካሄድ ያሁኑ የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ጉባዔው የሚመክርባቸው ዓበይት ጉዳዮች የድህነት ቅነሳና የምግብ ዋጋ መናር በወቅቱ በዓለም ያስከተለው ቀውስ ናቸው።

https://p.dw.com/p/E0Yy
የተመድ ዋና ጸሀፊ ፓን ኪ ሙን ጉባዔውን ሲከፍቱ
የተመድ ዋና ጸሀፊ ፓን ኪ ሙን ጉባዔውን ሲከፍቱምስል AP