1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ የፊልም ትርዒት በብራስልስ

ረቡዕ፣ መስከረም 20 2002

ትርኢቱ አለም አቀፉ ድርጅት ድሕነት፥ ማይምነት፥ በሽታና የፆታ ተባለጥን ለማጥፋት ወይም ለመቀነስ የቀየሰዉ መርሕ ተቀባይነት እንዲኖረዉ ለማድረግ ያለመ ነዉ

https://p.dw.com/p/Jurm
የተመድ የርዳታ አርማምስል dpa/DW

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የማአቱ (ሚሊኒየም) ግብ ያለዉን መርሕ በሕዝብ ዘንድ ለማስረፅ ያለመ አለም አቀፍ የፊልም ትርዒት ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ሲታይ ሰነበተ።ለአለፉት አስር ቀናት ለሕዝብ የቀረበዉ የፊልም ትርኢት አለም አቀፉ ድርጅት ድሕነት፥ ማይምነት፥ በሽታና የፆታ ተባለጥን ለማጥፋት ወይም ለመቀነስ የቀየሰዉ መርሕ ተቀባይነት እንዲኖረዉ ለማድረግ ያለመ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ እንደዘገበዉ ከተለያዩ ሐገራት በርካታ ፊልሞች የቀረቡበትን ትርዒት ያዘጋጁት የቢልጂግ ጥናታዊ ፊልም አዘጋጆች ማሕበር፥ የቤልጂግ የልማት ተራድኦ መስሪያ ቤትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ናቸዉ።

ገበያው ንጉሴ/ነጋሽ መሀመድ/አርያም ተክሌ