1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ- ፋኦ-ዓመታዊ ዘገባ

ሐሙስ፣ ኅዳር 29 1998

ከግብርናው ዘርፍ መፍታታት የሚጠቀሙትና የሚጎዱት ሀገሮች የትኞቹ ናቸው?

https://p.dw.com/p/E0e6
የፋኦ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሀርትቪክ ደ ሄን
የፋኦ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሀርትቪክ ደ ሄንምስል AP

በሚቀጥለው ሣምንት ሆንኮንግ ውስጥ የዓለም ንግድ ድርጅት በሚንስትሮች ደረጃ አንድ ጉባዔ ይከፍታል። በጉባዔው የሚሳተፉት ሀገሮች ተወካዮች በዶሀ የድርድር ዙር ላይ የተደረሱት ስምምነቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን ርምጃ ለማፋጠን ይቻል ዘንድ በዓለም ንግድ ላይ የተደቀኑትን ማከላከያ ሁኔታዎችን ለማንሣት ይሞክራሉ። የግብርናው ዘርፍ ጉባዔው በዋነኝነት የሚመክርበት ጉዳይ ይሆናል። ይኸው ጉባዔ ሊጀመሩ ጥቂት ቀናት ሲቀረው የተመ የምግብና የእርሻ ድርጅት፡ ፋኦ ባወጣው ዓመታዊው ዘገባው ላይ የግብርናው ዘርፍ ወደፊት ከሚፍታታበት አሠራር የትኞቹ የዓለም ሀገሮች ሊጠቀሙ ወይም ሊጎዱ የሚችሉ ይችላሉ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክሮዋል።