1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር የኢትዮጵያ ጉብኝት 

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 25 2009

የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከኢትዮጵያ መንግሥት ተደርጎላቸዋል በተባለዉ ግብዣ መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለፀ። የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነሩ በቆይታቸዉ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/2cEht
Schweiz UN High Commissioner for Human Rights Zeid Ra'ad al-Hussein
ምስል Reuters/P. Albouy

Ber. D.C (UN Human Rights Commissioner zu Besuch Äthiopien)/MMT - MP3-Stereo

ጉብኝታቸዉን አስመልክቶ የተቋሙ ቃል አቀባይ ለዶይቼ ቬለ እንዳስታወቁት ባለስልጣኑ የተቃዋሚ መሪዎችንና የመንግሥት ባለስልጣናትን አግኝተዉ ያነጋግራሉ። የዚህን ጉብኝት አላማ አስመልክቶ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሰብዓዊ መብትና የዓለም አቀፍ መብት መምህር በበኩላቸዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት፤ ተጠያቂነትን ለማስፈን በራሳችን መንገድ አጥርተን የሞተዉን ሰዉ ቁጥር ዘገባ አቅርበናል ለዘገባችን እዉቅና ስጡልን ለማለት ያሰቡበት ግብዣ ነዉ ይላሉ። ዝርዝሩን የዋሽንገተኑ ወኪላችን ልኮልናል።    


መክብብ ሸዋ

አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ