1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና ዝግጅት 

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 24 2010

ስሙ ጋድሳ ዋጊ ይባላል። ተወልዶ ያደገዉ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በሰበታ ከተማ እንደ ሆነ ይናገራል። ባለፈዉ ዓመት የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዶ ነጥብ ሳይሞላለት ሲቀር አሁን በአዲስ አባባ በሚገኘዉ በርፍት ቫል ዩኒቨርሲቲ የነርስነት ትምህርት በመከታተል ላይ እንደሚኝ ለዶይቼ ቬሌ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/2x3NU
Karte Äthiopien englisch

Students' National Exam preparation - MP3-Stereo

እንደ ጋዲሳ አስተያየት፣ በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው የፖለቲካ ቀዉስ በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ነበረዉ።

በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ወለጋ ዞን በነቀምት ከተማ ነዋሪ የሆነዉ ግን ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገዉ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ጋድሳን ያጋጠመዉ እድል በዚህ ዓመትም ብዙ ተማሪዎችን እንዳያጋጥማቸው  ይሰጋል። አንድ ለሰባት በሚል አደረጃጀት  አንድ በትምህርት ጎበዝ የሆነ ደከም ያሉትን ተማሪዎች እንደሚያስጠና ተማሪዉ ይናገራል።

ተማሪዉ የፀጥታ ሃይል ወታደሮች/በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ የሚገኙበት ሁኔታ በተማሪች ስነ-ልቦና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ ያምናል። ወታደሮች ወደ ካምፕ ሲመለሱ ብቻ የተማሪዎች ስነ ልቦና ሊረጋጋ እና ለፈተና የሚያደርጉት ዝግጅትም እንደሚሻሻል ይገምታል።

በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን በሻኪሶ ከተማ በዝህ ዓመት ለብዙ ግዜ ትምህርት በፖለቲካዉ አለመረጋጋት ምክንያት በተደጋጋም ሲቋረጥ እንደ ነበረ አንዲት የከተማው ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ ትናገራለች። እስከ ባላፈዉ ሳምንት ድረስ ትምህርት ለጊዜዉ ቢቀጥልም ፣ ከዛሬ ጀምሮ ግን መቋረጡን ገልጻለች። ምክንያቱም ተማሪዎች ከሌሎች የፖለቲካ ጥያቄዎች ጎን ለጎን የሚድሮክ ኩባንያ ወርቅ የሚያወጣበት ድርጊት  በነዋሪዎች ጤና እና በአከባቢው ላይ እያደረሰ ይገኛል የተባለዉን  ጉዳት በመቃወማቸው  መሆኑን አክላ አስረድታለች።

በዚሁ ጉዳይ ላይ በዶይቼ ቬሌ የዋትስአፕ ገፅ ላይ ስማቸዉን ሳይጠቅሱ ሁለት ግለሰቦች ከአማራ ክልል ከዳሴና ከባቲ አከባብ አስተያያታቸዉን የላኩልን ደግሞ የአገሪቱን የትምህርት ስረዓት በመተቸት፤ በጥረታቸዉ ለፈተናዉ እየተዘጋጁ እንደሚገኙ ጽፈውልናል። በኢትዮጵያ-ሶማሊ ክልል መምህር ነኝ ያሉት ደግሞ ፈተናዉ ለዓመታት በፈታኞች ሳይሆን በመምህራን እንደሚሰጥና ይህም የፈተናዉ ጥራት ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ እንደሚገኝ በፅሁፋቸዉ ገልጸዋል።

የጋድሳን የትምህርት ትዉልድ ያጋጠመዉ እድል አይነት በዚህ ዓመት ሌሎችን እንዳያጋጥም የሚምመለከታቸዉ የመንግስት ተቋማት ምን ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አጄንስ የሕዝብ ግኑኚነትና ኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረድ ሽፋ ናቸዉ። እሳቸዉ እንደምሉት የየፀጥታ ጉዳይ የምመለከተዉ የተቋቋመዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት መሆኑን የተናገሩት አቶ ሽፋ ኮማንድ ፖስቱ የተማርዎችን ስነ-ሊቦና ለመጠበቅ እንጅ ለመጉት እንዳልሆነ amክሎበታል።

ከግንቦት 22 እስከ 30፣ 2010 ዓም ይሰጣል ለሚባለው ለዚህ ብሔራዊ ፈተና አጄንስዉ በአጠቃላይ ወደ 1,5 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለፈተናዉ እንደመዘገበ፤ እንድሁም ከ50ሺህ እስከ 60 ሺህ ፈታኞችንና ተቆጣጣሪዎች ማዘጋጀቱን አቶ ረድ ገልፀዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ