1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ፓርቲዎቹ ድርድር ይቀጥሉ ብለዋል።

ሰኞ፣ ኅዳር 11 2010

ለጀርመን የጥምር መንግሥት ለመመሥረት ለሳምንታት ሲደረግ የነበረው ድርድር ትናንት እኩለ ሌሊት ያለ ውጤት ተበትኗል። የነፃ ገበያ አቀንቃኙ የነፃ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ፣ ኤፍ.ዲ.ፒ. ተወካዮች ድርድሩን ረግጠው ወጥተዋል።

https://p.dw.com/p/2nxOP
Deutschland Ende Jamaika-Koalition Sondierungsgespräche | Angela Merkel; Bundeskanzlerin
ምስል Reuters/A. Schmidt

ጥምር መንግሥት ለመመስረት የተደረገው ድርድር አልሰመረም

የፓርቲው መሪ ክርስቲያን ሊንደር እንዳሉት በተደራዳሪዎቹ መካከል የእምነት መሰረት አልነበረም። የድርድሩ ውድቀት ላለፉት 12 አመታት ጀርመንን የመሩትን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፈተና ውስጥ ጥሏቸዋል። ቀጥሎ የሚፈጠረው ነገር በግልፅ ባይታወቅም መራሒተ-መንግሥቷ አዲስ ምርጫ እንዲካሔድ የመወሰን ሥልጣን ካላቸው ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጋር ተገናኝተዋል። የጀርመን ጋዜጦች ለድርድሩ አለመሳካት ተጠያቂው ክርስቲያን ሊንደር እና ፓርቲያቸው ናቸው ሲሉ ይደመጣል። ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎች በድርድራቸው እንዲገፉበት ጥሪ አቅርበዋል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ

አርያም ተክሌ