1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተሰዳጆች መበራከትና የአፍሪቃ መሪዎች ቸልታ

እሑድ፣ ግንቦት 30 2007

ወደ አዉሮጳ ለመግባት ተመኝተዉ የተወለዱበትና የኖሩበትን አካባቢ እየተዉ የሚሰደዱ አፍሪቃዉያን ቁጥር ከዕለት ወደዕለት እየጨመረ መሄዱ እየታየ ነዉ። ተሰዳጆቹ ከየሀገራቸዉ የሚወጡበት የተለያየ ቢሆንም ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸዉ በራሳቸዉ ሀገር ብሩህ ተስፋ ማጣታቸዉ እንደሆነ ይታመናል።

https://p.dw.com/p/1Fc99
Flüchtlinge Mittelmeer Bootsflüchtlinge
ምስል Reuters/Marina Militare

የተሰዳጆች መበራከትና የአፍሪቃ መሪዎች ቸልታ

በአንድ ወገን የተሰዳጆቹ ቁጥር መበራከት በሌላ በኩል ደግሞ ወደአዉሮጳ ለመድረስ የሜድትራኒያንን ባህርን ለማቋረጥ ሲሞክሩ ለአደጋ መጋለጣቸዉ የአዉሮጳ ሃገራት መሪዎች አሳስቧል አደናግጧል። እነሱን ከመስጠም ለማዳንም ሆነ ሳይነሱ በደረሱበት መሸጋገሪያ ሀገር ለማስቀረት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የአብዛኞቹ ስደተኞች መፍለቂያ የሆነችዉ አፍሪቃ መሪዎች በተቃራኒዉ ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት የሰጡት አይመስልም። የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት እንወያይ መሰናዶ የአፍሪቃዉያን ስደተኞች መበራከትና የአፍሪቃ ኅብረትን ቸልታ ይመለከታል። ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ