1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተሳካው የቺሌው ህይወት የማዳን ዕርምጃ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 4 2003

ለ 69 ቀናት በማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው የቆዩትን 33 የቺሊ የማዕድን ሠራተኞች የማውጣቱ ስራ ያለ አንዳች እንከን ተጠናቋል ።

https://p.dw.com/p/PeFd
ምስል AP

የማዕድን ሰራተኞቹን ተራ በተራ በሚሳኤል መሰል ቱቦ ወደ መሬት የማውጣት የረቀቀ ተግባር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አስደምሟል ። የልብ አንጠልጣዩ ሂደት ውጤት ቺሊያውያንን እጅግ አስፈንድቋል ። ፕሬዝዳንታቸውን አኩርቷል ። ከማዕድን ሰራተኞቹ አብዛኛዎቹ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ