1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተሸናፊው ታጣቂ ቡድን ልጆች እጣ-ፈንታ

ማክሰኞ፣ ጥር 1 2010

ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በሶርያ እና በኢራቅ ከገጠመው ሽንፈት በኋላ ለጀርመን ራስ ምታት የሆነ ጉዳይ ተፈጥሯል። ቡድኑን የተቀላቀሉ እና ከታጣቂዎቹ ጋር ትዳር የመሰረቱ አብዛኞቹ እንስቶች የልጅ እናት ሆነዋል። የልጆቹ እጣ-ፈንታ ምን ይሆናል?

https://p.dw.com/p/2qafi
Syrien Frau und Kind eines vermeintlichen IS Kämpfers in Rakka
ምስል Getty Images/AFP/B. Kilic

በመቶዎች የሚቆጠሩ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል

አንዳንዶቹ ወደ ኢራቅ እና ሶርያ አምርተው በታጣቂ ቡድኑ የጦር አውድማዎች ሲሰለፉ ልጆቻቸውን ጭምር ይዘው ሔደዋል። በጦር አውድማዎች ተሰልፈው የተዋጉ ታጣቂዎች ሚስቶች እና ልጆቻቸው መፃዒ እጣ-ፈንታ ምን ይሆናል? የጀርመን ፌደራል መንግሥት በመቶዎች የሚቆጠሩ የታጣቂዎች ልጆች ወደ አገሪቱ እንደሚመለሱ ይጠብቃል። 
ይልማ ኃይለሚካኤል /ኡታ ሽታይቬኸር
አርያም ተክሌ