1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መኢአድ፣ ሰማያዊና ኢራፓ ስለፖለቲካ ቀውሱ መግለጫ አውጥተዋል

ረቡዕ፣ የካቲት 14 2010

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታን አስመልክቶ የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በበኩሉ ኢትዮጵያ ላለችበት አጣብቂኝ መፍትሔ ነው ያለውን ጠቁሟል።

https://p.dw.com/p/2t6aQ
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታን አስመልክቶ የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ፓርቲዎቹ አሁን በሀገሪቱ ላለው የፖለቲካ ችግር መፍትሄ ለማበጀት በሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ያካተተ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በበኩሉ ኢትዮጵያ ላለችበት አጣብቂኝ “ብሔራዊ መግባባት ከመፍጠር  ውጭ አማራጭ የለም” ብሏል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ያጠናቀረውን ዝርዝር ዘገባ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ፡፡ 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ተስፋለም ወልደየስ

ኂሩት መለሰ