1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሠላማዊ ሠልፍ መታገድ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2007

የአዲስ አበባ መስተዳድር ዕዉቅና መንፈጉን ሕገ-ወጥ ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲዎቹ በዕቅዳቸዉ እንዲሚቀጥሉበት አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/1DyIM
Demonstration der Semayawi-Partei in Addis Ababa Äthiopien 22.09.2013
ምስል DW

የጋራ ጥምረት የመሠረቱት የኢትዮጵያ መንግሥት ዘጠኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመጪዉ ሳምንት ማብቂያ አዲስ አበባ ዉስጥ እንዲደረግ ያቀዱትን የተቃዉሞ ሠልፍ የከተማይቱ መስተዳድር መከልከሉን የፓርቲዎቹ አስተባባሪ አስታወቁ።የጋራ ጥምረቱ አስተባባሪና የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እንዳስታወቁት መስተዳድሩ ለታቀደዉ ሠላማዊ ሠልፍ ዕዉቅና የነፈገዉ ሠልፉ ሊደረግ የታቀደበት ሥፍራ የልማት ሥራዎች የሚከናወኑበት፤የመንግሥትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚገኝበት ነዉ በሚል ሰበብ ነዉ።የአዲስ አበባ መስተዳድር ዕዉቅና መንፈጉን ሕገ-ወጥ ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲዎቹ በዕቅዳቸዉ እንዲሚቀጥሉበት አስታዉቀዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ