1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቋረጠው የሶሪያ የሰላም ንግግር

ሐሙስ፣ ጥር 26 2008

የሶሪያ ተቃዋሚ ቡድን የሶሪያ መንግሥት የአየር ድብደባ ለማቆም እስካልተስማማ ድረስ ወደ ጄኔቫው የሰላም ድርድር እንደማይመለስ አስታውቋል ።የአሁኑ የሰላም ንግግር አምስት ዓመት የዘለቀውን የሶሪያ ደም አፋሳሽ ግጭት የማስቆም ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት ነበር።

https://p.dw.com/p/1HpwV
Genf Syrien Konferenz HNC Vertreter Opposition Mistura
ምስል Reuters/D. Balibouse

[No title]


ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ በተዘዋዋሪ ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ ሲካሄድ የነበረው የሶሪያ የሰላም ንግግር መቋረጡን አደራዳሪው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናንት አስታውቋል ።ንግግሩ መቋረጡ የተነገረው የሶሪያ መንግሥት ከቱርክ ጋር ወደ ሚያዋስነው ሁለተኛ የሶሪያ ትልቅ ከተማ አሌፖ የሚወስደውን ቁልፍ መጋቢ መንገድ መቁረጡን ካሳወቀ በኋላ ነው ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ ልዩ ልዑክ ስታፋን ደ ሚስቱራ የሰላሙ ንግግር ከ20 ቀናት በኋላ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።በድርድሩ የተካፈለው ዋነኛው የሶሪያ ተቃዋሚ ቡድን ግን የሶሪያ መንግሥት የአየር ድብደባ ለማቆም እስካልተስማማ ድረስ ወደ ጄኔቫው የሰላም ድርድር እንደማይመለስ አስታውቋል ።የአሁኑ የሰላም ንግግር አምስት ዓመት የዘለቀውን የሶሪያ ደም አፋሳሽ ግጭት የማስቆም ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት ነበር። ስለተቋረጠው የሶሪያ የሰላም ንግግር የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግረነዉ ነበር።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ