1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተባባሰው የሶማሊያ ውጊያ

ረቡዕ፣ ግንቦት 5 2001

ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ በመንግስት ወታደሮች እና በመንግስት ደጋፊ ኃይላት እንዲሁም አልሸባብ በተሰኘው ደፈጣ ተዋጊ ቡድን መካከል ካለፈው ሀሙስ አንስቶ የሚካሄደው ውጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ።

https://p.dw.com/p/HpQY
ምስል AP

በዚሁ ውጊያም ከመቶ በላይ ሰዎች ተገድለዋል ፤ ወደ ሶሶት መቶ የሚጠጉ ቆስለዋል ፣ሀያ ሰባት ሺህ የሚደርሱ ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል ። ከአካባቢው በሚወጡ ዘገባዎች መሰረት መዲናይቱን መቅዲሾን ለመያዝ የሚዋጋው አልሸባብ በአሁኑ ጊዜ አብዛኛውን የከተማይቱን ክፍል ተቆጣጥሯል ። ባለፉት ሰባት ቀናት በሶማሊያ ተባብሶ ሰለቀጠለው ውጊያ ሂሩት መለሰ ሶማሊያዊውን ጋዜጠኛ ሙስጠፋ አብዲ ኑርን አነጋግራ ተከታዪን ዘገባ አጠናቅራለች ። ።

ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ