1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቸገሩ ከያንያንን እንርዳ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 2005

በአገራችን የኪነ-ጥበብ መድረክ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ እና በአሁኑ ወቅት በበሽታ በእድሜ አቅም አንስዋቸዉ ተረስተዉ የሚገኙ ታዋቂ ሰዎችን ለመርዳት በጀርመን አገር የተቋቋመዉ ማዕከል የዛሬ 10 ቀን ግድም ከኢትዮጵያ 6 ታዋቂ የመድረክ ሰዎችን ጋብዞ በተለያዩ የአዉሮጳ አገራት የመጡ ከያንያን በተገኙበት ባህላዊ የመድረክ ዝግጅትን አካሂድዋል።

https://p.dw.com/p/1964Z
Titel: Aselefech Ashene, bekannteste äthiopische Künstlerin Äthiopiens auf einer großen musikalischen Gala in Frankfurt Kelkheim. Gesellschaft zur Förderunng der Äthiopischen künste e.V Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW 2013
ምስል DW/A. Tadesse Hahn

በዛሬዉ ዝግጅታችን በመድረኩ ከተገኙ ከያንያን መካከል አንጋፋዋን አርቲስት አሰለፈች አሽኔን እና ፀሃፊ አብርሃም አስመላሽን እንዲሁም የማህበሩን እንቅስቃሴ እንቃኛለን፤ ባለፈዉ ሰሞን በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ታዋቂ የመድረክ ሰዎች ተካፋይ የሆኑበት እዚህ በጀርመን በፍራንክ ፈርት ከተማ የተካሄደዉ ታላቅ የባህል ሙዚቃ ምሽት ላይ ፀሃፊ ተዉኔት አያልነህ ሙላት አርቲስት ዳዊት ይፍሩ አንጋፋዋ አርቲስት አሰለፈች አሽኔ ይገኙበታል። አንጋፋና ወጣት የመድረክ ሰዎችን ያሳፈዉ የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ፤ የኢትዮጵያን ስም ያስጠሩ አሁን ተረስተዉ ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ለመረዳጃ እንደሆነ ተነግሮአል። በጀርመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኪነ-ጥበብ ማዕከል ተጠሪ አቶ ተፈሪ ፈቃደ ማዕከሉ የተቋቋመዉ ይላሉ፤

Titel: Aselefech Ashene, bekannteste äthiopische Künstlerin Äthiopiens auf einer großen musikalischen Gala in Frankfurt Kelkheim. Gesellschaft zur Förderunng der Äthiopischen künste e.V Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW 2013
ምስል DW/A. Tadesse Hahn

በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ አጫጭር ድራማዎች መነባንብ፤ ግጥምና ሙዚቃ የቀረበበት እንደሆነ ተገልጾአል። አንጋፋዋ የከያኒ አሰለፈች አሽኔ በቦታዉ ላይ በመገኘትዋ እና ለደከሙ የመድረክ ሰዎች ማሰባሰብያ ዝግጅት ላይ በመሳተፍዋ ደስተኛ መሆንዋን እንዲህ ገልጻልናለች፤ በጀርመን የሚገኘዉ የኢትዮጵያዉያኑ ባህላዊ መድረክ ሌላዉ ተጋባዥ እንግዳ አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ነዉ፤ በአዝናኝና እና በቁም ነገር አዘል ቀልዶቹ የሚታወቀዉ አብርሃም አስመላሽ በአደረበት ሕመም ምክንያት ከመድረክ ከተለየ ዓመታትን አስቆጥሮአል። የባህል ማዕከሉ ለአብርሃም አስመላሽ ህክምና ገንዘብ ማሰባሰብያ በሳምንቱ መጨረሻ ፍርንክፈርት ላይ መድረክ አዘጋጅቶአል። አብርሃም ከሚያቀርበዉ መነባንቡ መካከል አንድ ሁለቱን አካፍሎናል፤ ዝግጅቱን ያድምጡ!በሌላ በኩል የመድረክ እንቁዋ አርቲስት አሰለፈች አሽኔ በፍርንክፈርቱ መድረክ የአገር ፍቅር ትዝታዉ፤ የተሰኘዉን ዜማ አስደምጣለች፤ ለዝግጅት ክፍላችምን ዳግም ተጫዉታ ለአድማጮቻችን እንድናስደምጥላት ጠይቃናለች። መዝሙርን ለመዘመር ሥትል በ 1947 ዓ,ም ወደ አገር ፍቋር ትያትር የገባችዉ አንጋፋዋ አርቲስት አሰለፈች አሽኔ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ብሄራዊ የኪነጥበብ ማዕከል ጥራ ስር ሆና ደጋፊ አጥተዉ የሚገኙትን አንጋፋ ሞያ ባልደረቦችዋን በመርዳት ላይ ትገኛለች

አንጋፋ ስመ ጥር ኢትዮጵያዉያን ለወጣቱ ትዉልድ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ሊታሰብ የሚገባዉና፤ እርዳታ የሚሹ አንጋፋ ባለሞያዎች፤ ሊበረታቱ እና ሊደገፉ የሚገባ ይመስለናል። ለዝግጅቱ መሳካት በጀርመን ፍራንክፉርት የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኪነ-ጥበብ ማዕከል ላደረግልን ትብብር እናመሰግናለን።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ