1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተወካዮች ም/ቤት የ2005 በጀት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 5 2004

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ 2005 ዓም በቀረበለት የአንድ መቶ ሠላሳ ሰባት ነጥብ ስምንት ቢልዮን ብር በጀት ላይ ዛሬ መከረ። በዕቅድ ከቀረበው በጀት መካከል ብዙውን ሀገሪቱ ካለውጭ ርዳታ በራስዋ ገቢ እንደምትሸፍን

https://p.dw.com/p/15Crh
Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Das Parlamentsgebäude in Äthiopiens Hauptstadt Addis Abeba Thema: Am 23.Mai wählen 32 Millionen registrierte Äthiopier ein neues Parlament sowie die Vertreter der State Councils. 547 Sitze sind zu vergeben. Die - umstrittene - Einwohnerzahl der 9 + 2 Regionen Äthiopiens bestimmt die Zahl der Sitze. Schlagwörter: Parlamentswahl Äthiopien 2010, Parlament, Sitze
ምስል DW

የገንዘብና የኤኮኖሚ ልማት ሚንስትር አቶ ሱፊያን አህመድ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በጀመረችው የትራንስፎርሜሽን እና ዕድገት ዕቅዷ መሠረት፡ በርካታ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ልማቶች ማስመዝገቧን ሚንስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ ቢያመለክቱም፡ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ያደረገችው ሙከራ ግን የተፈለገውን ውጤት እንዳላስገኘ አስረድተዋል። ይሁን እንጂ፡ ተመዘገበ የተባለው የልማት ሥራ በሰዎች የኑሮ ሁኔታ ላይ ለውጥ እያመጣ አለመሆኑን ብቸኛው የተቃዋሚ እንደራሴ አቶ ግርማ ሰይፉ ገልጸዋል።

ታደሰ እንግዳው
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ