1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተገኘዉ የአዉሮፕላን ስባሪ ከየት መጣ?

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2007
https://p.dw.com/p/1GA8z


ከማሌዥያ ኳላላምፑር ወደ ቻይና ፔኪንግ 239 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የመንገደኞች ማመላለሻ አዉሮፕላን ከጠፋ አንድ ዓመት ከመንፈቅ አስቆጠረ። ከማዳጋስካር 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ሪዩኒየን ደሴት የባህር ጠረፍ ላይ ከተገኘዉ የአዉሮፕላን ስባሪ ምናልባት የጠፋዉ የማሌዢያ አዉሮፕላን አካል ሳይሆን እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ። ምንም እንኳ እስካሁን ማረጋገጫ ባይሰጥም። የዉቅያኖስ ዉኃ ዝዉዉር አጥኚዎች እንደሚሉት ደግሞ የተገኘዉ የአዉሮፕላን ስባሪ ይወድቃል ተብሎ ከታሰበበት በ 17 ወራት ጊዜ ዉስጥ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ መገኘቱ የሚታመን ነዉ ። በዕለቱ ዝግጅታችን የተሰወረዉን የማሌዥያ አዉሮፕላን MH370 ጉዳይ የባህር ዉኃ ንቅናቄ አጥኝዎች ትንታኔን እንቃኛለን።