1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈናቃይ መበራከትና የርዳታው ጥረት

እሑድ፣ ኅዳር 19 2014

አንድ ዓመት ያለፈው ትግራይ ላይ የተለኮሰው ጦርነት አድማሱን አስፍቶ በአፋር እና አማራ ክልል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀሉ የርዳታ ፈላጊው ቁጥር በሚሊየኖች ሆኗል። በጦርነቱ ምክንያት ከሰሜን ወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች እያስተባበሩ ይደግፉ የነበሩ ዛሬ እነሱም ርዳታ ጠባቂዎች መሆናቸው ታይቷል።

https://p.dw.com/p/43YRT
Äthiopien | Vereilung von Hilfsgütern
ምስል Mulugeta Ayene/AP/picture alliance

ውይይት

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አሉ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጎሳን መሠረት ባደረገ ጥቃት ምክንያት በምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በምሥራቁ የሀገሪቱ ክፍል በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው አንዳንዶቹም በያሉበት ርዳታ ለመጠበቅ ተገድደዋል። የትግራዩ ጦርነት አድማሱን አስፍቶ ወደ አማራ እና አፋር ክልል በመዝለቁም የተፈናቃዩ ቁጥርም ሆነ የዕለት ደራሽ ርዳታ ፈላጊው መጠን በጣም ጨምሯል። መንግሥት ለእነዚህ ወገኖች ርዳታ ለማቅረብ የሚችለውን እያደረገ መሆኑን ይገልጻል። ችግሩ ያሳሰባቸው በጎ ፈቃደኞችም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ኅብረተሰቡን በማስተባበር ሲንቀሳቀሱ ይታያል። አንዳንዶች እንደውም ከውጭ ከመጠበቅ ራስን መቻል ያዋጣል በሚል ጥረቱን ያበረታታሉ። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት ያካሄደው ውይይት በሀገር ውስጥ የተፈናቃዩ መበራከት፣ ለተቸገሩት ለመድረስ የሚደረገው የመንግሥትም ሆነ የበጎ ፈቃደኞች ጥረት ምን ይመስላል? በሙሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። 

ሸዋዬ ለገሠ

ታምራት ዲንሳ