የተፈናቃዮች መመለስ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስተዉ በነበሩ ግጭቶች ከቤት ንብረታቸዉ ከተፈናቀሉ ሰዎች አብዛኞቹ ወደየቀያቸዉ መመላሳቸዉን የሐገሪቱ የአደጋ ስጋት ምክትል ኮሚሽነር አስታወቁ።ምክትል ኮሚሽነር መኮንን ለገሰ ከጌድዮና ከምዕራብ ጉጂ ዞኖች ተፈናቅለዉ ወደየአካቢያቸዉ የተመለሱ ነዋሪዎችን ለመርዳት የተዘጋጀ ፕሮጀክት ሐዋሳ ዉስጥ ይፋ ሲሆን አክለዉ እንዳሉት መንግሥት በየአካባቢዉ የሕግ የበላይነትን እያስከበረ ነዉ።ትናንት ይፋ የሆነዉ ፕሮጄክት ከሁለቱ ዞኖች ተፈናቅለዉ ለነበሩ ከ50 ሺሕ የሚበልጡ ነዋሪዎችን ይረዳል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ