1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርክና የአርሜንያ ስምምነት

ሰኞ፣ ጥቅምት 2 2002

ቱርክ እና አርሜንያ በርካታ አመታት ያቆጠረ ጠብና ዉዝግባቸዉን ለማስወገድ ባለፈዉ ቅዳሜ ያደረጉት ስምምነት ድጋፍም ተቃዉሞም ገጥሞታል።የሥምምነቱን የፊርማ ሥነ-ሥርዓት በታዛቢነት የተከታተሉት የዩናይትድ ስቴትስ፥ የፈረንሳይ፥ የሩሲያና የአዉሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት፣

https://p.dw.com/p/K4nP
ምስል dpa

ሁለቱ ሐገሮች መስማማታቸዉ ላካባቢዉ ሰላም ይረዳል በማለት ሥምምነቱን ደግፈዉታል።የአርሜንያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ዉጪ ሐገር የሚኖሩ የሐገሪቱ ዜጎች ግን ቱርክ ላደረሰችዉ በደል ይቅርታ ሳትጠይቅ መንግሥታቸዉ ከቱርክ ጋር መስማማቱን ተቃዉመዉታል።ነብዩ ሲራክ ከጄዳ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ነብዩ ሲራክ ተክሌ የኋላ፣ነጋሽ መሐመድ