1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርክ ምርጫ ዉጤት እና ከአዉሮጳ ጋር ያላት ግንኙነቷ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2007

ባለፈዉ እሁድ በቱርክ የተደረገዉ የእንደራሴዎች ምርጫ ባለፉት 13ዓመታት በስልጣን ላይ የነበረዉ የፕሬዝደንት ኤርዶኻን የፍትህና ልማት በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ AK ፓርቲ ብቻዉን መንግሥት ለመመሥረት የሚያበቃ የፓርላማ መቀመጫ አላስገኘለትም።

https://p.dw.com/p/1Fe7r
Türkei Parlamentswahl
ምስል Getty Images/A. Altan

[No title]

ፕሬዝደንት ራሲፕ ጣሂብ ኤርዶኻን በጎርጎሪዮሳዊዉ 2002ዓ,ም ፓርቲዉን ከመሠረቱ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ወቅቶች እስከ2014ምርጫ ድረስ የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር በመሆን ቱርክን መርተዋል። በአሁኑ ምርጫ ፓርቲያቸዉ ከጠቅላላዉ 550 የምክር ቤት መቀመጫ ሁለት ሶስተኛዉን ቢያገኝ ኖሮ ሀገሪቱን ለፕሬዝደንቱ ይበልጥ ስልጣን ለሚሰጠዉ ወደፕሬዝደንታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመቀየር እቅድ ነበራቸዉ። ምርጫዉ ዓለም አቀፍ መስፈርትን ያሟላ እንደነበር ቢነገርለትም ቱርክን ከአዉሮጳ ኅብረት ለመቀላቀል የሚያበቃት አይመስልም።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ