1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርክ ትብብር እና የአውሮጳ ኅብረት ጥያቄ

እሑድ፣ ጥቅምት 7 2008

ቱርክ ከአውሮጳ ኅብረት የቀረበላትን ከተለያዩ ሃገራት የሚመጡ ስደተኞችን በሀገሯ አስቀርታ የማስተናገድ ጥያቄ በመተግበር ከተባበረች ከአውሮጳ ኅብረት ጋር የመቀራረቧ ሒደት በአዲስ መልክ እንደሚፋጠን ተገለጠ።

https://p.dw.com/p/1Gq8F
Istanbul Merkel Besuch Davutoglu
ምስል Reuters/B. Kilic

የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ቱርክ ኢስታንቡል ውስጥ ባደረጉት ንግግር ፤ቱርክ የአውሮጳ ኅብረት አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ በዚህ ዓመት አዲስ የመደራደሪያ ምዕራፍ መክፈቱን ገልጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለቱርክ ዜጎች የቪዛ አሰጣጡ ቀለል ያለ እና የተቀላጠፈ እንዲሆን መንገድ እንደሚያመቻቹ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተናግረዋል። በአፀፌታው ታዲያ ቱርክ ስደተኞች ወደ ሀገሯ የሚላኩበትን መንገድ እንድታመቻች አንጌላ ሜርክል ከቱርክ ጠቅላይ ሚንሥትር አኅመት ዳቩቶሉ ጋር ባደረጉት ንግግር ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሀገራቸው ቱርክ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን በመቆጣጠር ጀርመንን እንደምትተባበር ቃል ገብተዋል። ሆኖም «የሶሪያ ግጭት መፍትኄ ሳይበጅለት የስደተኞች ቀውስን መፍታት አይቻልም» ሲሉ አክለዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ