1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱኒዝያ አክራሪ ሙስሊሞች መጠናከር

ሐሙስ፣ ነሐሴ 5 2003

በቱኒዝያ ከጥቂት ወራት በፊት ከተካሄደው የጃስሚን ዓብዮት በኋላ በርካቶች በሀገሪቱ የሚገኙትን አክራሪ ሙስሊሞችን በብዛት እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።ተሰምቶዋል።

https://p.dw.com/p/RfGN

አክራሪዎቹ ሙስሊሞች ከአል ቓይዳ ጋ ግንኙነት እንደሌላቸው ቢያስታውቁም፡ በብዙኃኑ የሀገሪቱ ህዝብ ዘንድ ስጋት መፍጠራቸው አልቀረም።
በቱኒዝያ መዲና ቱኒስ በሚገኘው በሀገሪቱ መስራች እና ከ 1957 እስከ1987 ዓም ሀገሪቱን በመሩት የመጀመሪያ መሪ ፕሬዚደንት ሀቢብ ቡርጊባ ስም በሚጠራው አደባባይ ይወያዩ የነበሩ ሰፊ ጀለቢያ የለበሱና ጺማቸውን በረጅሙ ያሳደጉ ጥቂት ወንዶች በቱኒዝያ መንግስት እና ሀይማኖት ተለያይተው የሚሰሩበት ሁኔታ ህብረተሰቡን አበላሽቶዋል በሚል በጣም ወቅሰዋል። ይህ ዓይነቱ ግልጽ ወቀሳ በመንግስቱ ተግባር እና በህዝቡ ማህበራዊ ኑሮ ላይ ሀይማኖት ተጽዕኖ እንዳይሳርፍ ትጥር በነበረችው ቱኒዝያ ውስ ከጥቂት ወራት በፊት በፍጹም የማይታሰብ ነበር፤ ምክንያቱም የቱያኔው የሀገሪቱ የስለላ ድርጅት ሰዎቹን ወዲያው ያስራቸው ነበር።
ሀይማኖትን መሰረት ያላደረገ የመንግስት ስርዓትን የተከተሉ ፕሬዚደንት ሀቢብ ቡርጊባ በሀገራቸው የፆታ እኩልነትን እንዲኖር እና ቱኒዝያንም ዘመናይ ለማድረግ ይጥሩ ነበር። ይኸው ጥረታቸው ከአክራሪ ሙስሊም ኃይላት አኳያ ስሃት ስለተደቀነበት ቡርጊባ እዚህኑ ኃይላት በግልጽ መጨቆናቸው ይታወሳል። ይሁንና፡ ከጃስሚን ዓብዮት እና ተተኪያቸው ፕሬዚደንት ዚኔ ኤል አቢዲን ቤን አሊ ባለፈው ጥር 14 ፡ 2011 ዓም ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ አክራሪዎቹ ሙስሊሞች እንደገና በሀገሪቱ ፖለቲካ እና አደባባይ በይፋ ተመልሰዋል።

Protestieren in der Avenue Habib Bourguiba
ምስል DW

አክራሪ ሙስሊሞችን በሩቁ
በአሁኑ ጊዜ ሀቢብ ቡርጊባ አደባባይ ባሉ ሻይ ቤቶች የሚዝናኑት በጃስሚን ዓብዮት ወቅት በየቀኑ ለተቃውሞ አደባባይ ይወጡ የነበሩት ዘመናዮቹ ወጣትዋ ሳይሪን ቤልሄዲ እና ጓደኞችዋ ጺማሞቹን ሙስሊሞች ብዙም አያምኑዋቸውም፡ እንዲያውም እንደሚፈሩዋቸው ነው የሚናገሩት። አክራሪዎቹ ሙስሊሞች ስልጣን የሚይዙበት ድርጊት ሀገሪቱን በጣም ወደኋላ እንደሚመልሳት ገልጸዋል።
ወጣቶቹ ጺማሞቹን ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን፡ በተለይ በሀገሪቱ ሰፊ ተወዳጅነት ያገኘውንም ም የኤናሀዳን ፓርቲ አብዝተው ይፈራሉ። ለብዙ አሰርተ ዓመታት በሀገሪቱ በህግ ታግዶ የነበረው የኤናሀዳ ፓርቲ አሁን እንደገና በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ በግልጽ ጣልቃ መግባቱ አሳስቦዋቸዋል።
ጉብኝት በኤናሀዳው ፓርቲ መሪ ዘንድ
የአክራሪ ሙስሊሞች የኤናሀዳ ፓርቲ መሪ የሰባ ዓመቱ ራሺድ ጋኒቺ ሲሆኑ፡ በወግ አጥባቂዎቹ ሙስሊም ቡድኖች ዘንድ ከፍተኛ አመለካከት ያተረፉ ሰው ናቸው። የዓለም አቀፉ የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድናት ምክር ቤት አባል የሆኑት ጋኑቺ የሚያዘጋጁዋቸው ጽሑፎች ለዓለም አቀፉ የእስልምና መድረክ ትልቅ ትርጓሜ ይዘዋል። በፕሬዚደንት ቡርጊባ ዘመንም በፖለቲካው መድረክ በሰፊው ይንቀሳቀሱ የነበሩት ራሺድ ጋኑቺ ብዙ ጊዜ የመታሰር ዕጣ ገጥሞአቸዋል። የጃስሚን ዓብዮት ካበቃ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከሀያ ዓመት በላይ በስደት ከኖሩባት ከለንደን ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
እንግዶቻቸውን ከቱኒስ ወጣ ብሎ በሚገኝ እድ ዘመናይ ቤት የሚቀበሉት ጋኑቺ በፓርቲያቸው አኳያ የሚሰማው ፍርሀት የቀድሞው ፕሬዚደንት ቤን አሊ የፖለቲካ ተቀናቃኛቸውን ለማጥፋት ሲሉ ያስፋፉት ፍርሀት ነው ሲሉ ስጋቱ ትክክለኛ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል። የኤናሀዳ ፓርቲያቸው ዓላማ ህብረተሰቡን ከቤን አሊ የቀድሞው መንግስት ርዝራዦች ለማጽዳትና ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚታይበት ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ መንግስት ማቋቋም ነው። የቱኒዝያ ዜጎችም ሆኑ ምዕራቡ ዓለም በኤናሀዳ ፓርቲ አኳያ ስጋት ሊያድርበት እንደማይገባ ጋኑቺ አስገንዝበዋል።

Chef der Nahda Partei Rachid Al-Ghannoushi
ምስል DW
Flanieren in der Avenue Habib Bourguiba
ምስል DW

እስላማዊ መንግስት የመመስረት ህቡዕ አጀንዳ ይኖረው ይሆን?
ጋኑቺ ፓርቲያቸው ከአል ቓይዳ ጋ በፍጹም ግንኘት እንደሌለው ገልጸዋል። የአል ቓይዳ ተግባራት ህጋዊ ሳይሆኑ የሽብር ተግባራት ናቸው። አል ቓይዳ በቱኒዝያ እና በግብጽ በተካሄዱት ሰላማዊ ዓብዮት አንጻር እስከዛሬ ባካባቢው ካሉት በሙስና በተዘፈቁት መንግስታት መካከል አንዱንም ከስልጣን ማውረድ አለመቻሉንም ጋኑቺ አክለው አስረድተዋል። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ እስልምና እና እስላማውያን ንቅናቄዎች የመስከረሙ አንድ ጥቃት ባእስከተለው መዘዝ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። ከመስከረም አንድኡ የአሸባሪዎች ጥቃት በኋላ በምዕራቡ የሚገኙ ውሁዳን ሙስሊም ቡድኖች ባጠቃላይ በሽብር እንደሚጠረጠሩ እና ሁሌም የፖሊስ ክትትል እንዳረፈባቸው ጋኑቺ አክለው ተናግረዋል።

Tunis Demonstrieren für die Freiheit
ምስል DW

ከመስከረም አንዱ ጥቃት በስተጀርባ የነበረውን ዓላማ መልካም ነበር መባሉ

Tunis Demonstrieren vor dem Stadttheater.
ምስል DW

የኤናሀዳ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሪዳ ቤልሀዥም ቢሆኑ ፓርቲያቸውን አል ቓይዳን ከመሳሰሉ አክራሪው ሙስሊሞች ቡድኖች በግልጽ አልራቁም። በዚህ ፈንታ ከመስከረም አንዱ ጥቃት በስተጀርባ የነበረውን ዓላማ መልካም እንደነበር ቤልሀዢ አመልክተዋል። ይሁንና፡ ይኣላሉ ቤልሀዢ፡ ሙስሊሞች ልክ እንደ ምዕራባውያኑ የዓላማቸውን ትክክለኝነት ለማስረዳት የሚችሉበት የመገናኛ ብዙኃን ዘዴ ስለሌላችው ጥቃቱ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፎዋል። የፓርቲያቸው ኤናሀዳ ዓላማም በቱኒዝያ እስላማሚውን ህግ መሰረት ያደረገ መንግስት ስርዓት መፍጠር መሆኑን በስሜትት ገልጸዋል። ሳይሪን እና ጓደኞችዋ ግን ብዙኃኑ የቱኒዝያ ዜጎች በንዲህ ዓይነት ቱኒዝያ ውስጥ መኖር እንደማይፈልጉ ይናገራሉ። አክራሪዎቹ ሙስሊሞች ስልጣን ከያዙ ያኔ ሁሉም ሀገር ለቆ መሰደድ ይገደዳል የምትለው ሳይሪን ከጥቂት ወራት በፊት ያካሄዱት ዓብዮትም መና እንደሚቀር አስታውቃለች።

ኻሊድ ኤል ካውቲት
አርያም ተክሌ