1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱኒዝያ የሰብዓዊ ቀውስ ተከላካይ ግብረ ኃይል ምሥረታ ጥያቄ

እሑድ፣ መስከረም 27 2005

የቱኒዝያ ፕሬዚደንት ሞንሴፍ ማርዙኪ በሺዎች የሚቆጠሩ ተስፋ የቆረጡና በትናንሽ ጀልባዎች ወደ አውሮጳ ለመግባት የሚሞክሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን ሞት ላስከተለው የሰብዓዊ ቀውስ መፍትሔ የሚያፈላልግ አንድ ያካባቢ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/16M01
ምስል picture alliance / dpa

የቱኒዝያ ፕሬዚደንት ሞንሴፍ ማርዙኪ በሺዎች የሚቆጠሩ ተስፋ የቆረጡና በትናንሽ ጀልባዎች ወደ አውሮጳ ለመግባት የሚሞክሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን ሞት ላስከተለው የሰብዓዊ ቀውስ መፍትሔ የሚያፈላልግ አንድ ያካባቢ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ጠየቁ። ቱኒዝያዊው ፕሬዚደንት ይህን ጥያቄ ያቀረቡት የአውሮጳውያን እና የሰሜን አፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በሞልታ መዲና ቫሌታ ባካሄዱት ስብሰባ ማብቂያ ላይ ነበር። ግብረ ኃይሉ የአውሮጳውያን እና የሰሜን አፍሪቃ ሀገራት ውጭ እና የሀገር ውስጥ ሚንስቴሮች፡ እንዲሁም፡ ያካባቢ አካላት እያካሄዱት ያለውን ሰብዓዊ ርዳታ የመስጠቱን ሥራ ማስተባበበር እንደሚኖርበት ፕሬዚደንት ማርዙኪ አክለው አስረድተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን በባህር ሰምጠው የሚሞቱበት አሳዛኝ ሁኔታ በፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው ያስገነዘቡት ማርዙኪ፡ ባለመረጋጋት፡ በከፋው ድህነት እና በአፍሪቃ በሚታየው ከፍተኛው የወጣቶች ሥራ አጥነት ሰበብ ለተቀሰቀሰው ቀውስ በቅርቡ በቀላሉ መፍትሔ ማግኘት እንደማይቻል ግን ከማስጠንቅቅ ወደኋላ አላሉም።

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ