1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱኒዝያ የፓርላማ ምርጫ

እሑድ፣ ጥቅምት 16 2007

የአረብ አብዮት የትዉልድ ቦታ በሆነችዉ በቱኒዝያ ዛሬ የመጀመርያ የፓርላማ ምርጫ ሲደረግ ዋለ።

https://p.dw.com/p/1DcPg
Parlamentswahl in Tunesien 26.10.2014
ምስል Reuters/Anis Mili

በምርጫዉ አምስት ሚሊዮን ነዋሪ ድምፁን እንዲሰጥ ተጠርቶአል። በከፍተኛ ጥበቃና ቁጥጥር የተካሄደዉ የቱኒዚያ ምርጫ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ቤን አሊን በመቃወም ህዝባዊ አመጽ በተቀሰቀሰባት በትንሽዋ የቱኒዝያ ከተማ ሲዲ ቦዉዚዲም ምርጫ መካሂዱ ተመልክቶአል።

Parlamentswahl in Tunesien 26.10.2014
ምስል Reuters/Zoubeir Souissi

በምርጫዉ አብላጫ ድምፅን የሚያገኘዉ እስላማዊዉ «ኢናዳ ፓርቲ» እና ከሃይማኖት ገለልተኛ የሆነዉ «የኒዳ ፓርቲ» እንደሆን ይጠበቃል። በቱኒዝያ በሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ መከፋፈል በመኖሩ በሀገሪቱ አዲስ ፓርላማን የመመሥረቱ ሂደት ቀላል እንዳልሆነም ተነግሮአል። ከአራት ዓመት በፊት በቱኒዚያ የተነሳዉ የአረቡ አብዮት በተለያዩ ሀገራት መዛመቱ ይታወቃል። ይህ አብዮት ከተከሳተባቸዉ ሀገሮች መካከል ደግሞ ቱኒዚያ ከአብዮቱ አገግማ በአንጻራዊ የተረጋጋች እና ዲሞክሪያሳዊ መንገድን የያዘች ሀገር መሆንዋ ተነግሮላታል። በቱኒዝያ የፊታችን ህዳር 13 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚካሄድም ይጠበቃል።

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ