1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱኒዝያ ጊዚያዊ ሁኔታ

ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2005

በቱኒዝያ በእሥላማዊው መንግሥት እና በተቃዋሚዎች መካከል ውዝግቡ እየተባባሰ ሄዶዋል። የተቃውሞ ወገን ፖለቲከኛ መሀመድ ብራሂሚ እና በሣምንቱ መጨረሻም ሌላ የተቃዋሚ ቡድን ፖለቲከኛ ከተገደሉ ወዲህ ገዢው የኤናሀዳ ፓርቲ ከሀገሩ እና ከዓለም ዙሪያ ግፊት ተጠናክሮበታል። የተቃዋሚ ወገኖች አክራሪዎቹ ሙሥሊሞች እያጠናከሩት በመጣው የኃይል ተግባር

https://p.dw.com/p/19JKG
Tunisians take part in an anti-government demonstration on the Habib Bourguiba Avenue on July 26, 2013 in Tunis after the killing of the opposition politician Mohamed Brahmi. Tunisia marked a day of mourning on Friday after gunmen killed the leading opposition figure, sparking fresh political turmoil, protests and a general strike which took Tunis to near standstill. AFP PHOTO / FETHI BELAID (Photo credit should read FETHI BELAID/AFP/Getty Images)
ምስል Fethi Belaid/AFP/Getty Images

አንፃር መንግሥት ቁርጠኛ ርምጃ አልወሰደም በሚል አብዝተው ወቅሰውታል። በቱኒዝያ ባለፉት ጥቂት ጊዚያት ውስጥ አንድ የተቃዋሚ ወገን ፖለቲከኛ ሲገደል ብራሂሚ ሁለተኛው ናቸው። የብራሂሚ ቤተሰቦች እና የፓርቲያቸው አባላት ለግድያው ሳላፊስቶቹን ተጠያቂ አድርገዋል።

የቱኒዝያ ጠቅላይ ሚንስትር አሊ ላራዬድህ መንግሥታቸው ላረፈበት ግፊት እንደማይንበረከክ በመግለጽ የፊታችን ታህሳስ ምርጫ እንደሚደረግ አስታውቀዋል። ብዙ ቱኒዝያውያን መንግሥት ምርጫው ከአምሥት ወራት በኃላ እንዲደርግ መወሰኑ ሂደቶችን የማጓተተ ኣና በሠልጣን የሚቆየበትን ጊዜ ለማራዘም የተከተለው ሥልት አድርገው ተመልክተውታል።

በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ቱኒዝያውያን፣ የሙያ ማህበራት ጭምር ካለፊት ሳምንታት ወዲህ በመዲናይቱ ቱኒስ አደባባይ በመውጣት በኤናሀዳ ፓርቲ አንፃር ተቃዎሞ አሰምተዋል።
በዚሁ ወቅትም ከአክራሪ ሙስሊሞች ጋ ተደጋጋሚ የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ በማሰብ ነበር መንግስት የምርጫውን ዕለት ለ17፣12፣2013 የወሰነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ሕገ መንግሥታዊው ምክር ቤት የምርጫውን ሕግ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ይሁንና፣ የኤናሀዳ ፓርቲ ተወካዮች የሚገኙበት ምክር ቤት ከሕዝብ የነበረው መ ልካም ስም እያጣ መሄዱን የምክር ቤቱ እንደራሴ ካሜያስ ክሺሊ ገልጸዋል።
« ሕገ መንግሥታዊ ምክር ቤት ተዓማኒነቱን አጥቶዋል,። ይህ ምክር ቤት አንድመ ተስፋ አይሰጥም።ሕገ መንግሥት ማወጣት አልተሳካለትም በኤኮኖ ሚውም ሆነ በማህበራዊው ዘርፍ አንድ ደህና ውስጥ ማስመዝገብ አልተሳካለትም»
ከምክር ቤቱ ሁለት መቶ አሥራ ሰባት እንደራሴዎች መካከል አንድ ሦሰተኛው ከምክር ቤቱ ርቆዋል። ይህ ቁጥር ከጨመረ ምክር ቤቱ መበተኑ አይቀርም።
በ2011 የቀድሞው ፕሬዚደንት ቤን አሊ ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ የቱኒዝያውያኑ ሕይወት አልተሻሻለም። በአንፃሩ ተበላሽቶዋል። በሀገሪቱ መረጋጋት ተጓድሎዋል፣ ኤኮኖሚ ዕድገት አላሳየም፣ ስራ አጥነት ተስፋፍቶዋል። ቱኒዝያ ከዚህ ወዝግብ ትወጣ ዘንድ የተለያዩት ተቀናቃኝ ኃይላት ባንድነት ምስራት እንደሚጠበቅባቸው በመንግስቱ ውስጥ ከኤናሀዳ ጋ የተጣመረው የግራ ክንፍ ኤታካቶል ፓርቲ አባል መሀመድ ቤኑር ገልጸዋል።
«የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ያስፈልገናል። በዚሁ ውስጥም የተቃዋሚው ወገን በሰፊው መሳተፍ ይኖርበታል»

አነ አልሜሊንግ/አርያም ተክሌ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

Tunisians take part in an anti-government demonstration on the Habib Bourguiba Avenue on July 26, 2013 in Tunis after the killing of the opposition politician Mohamed Brahmi. Tunisia marked a day of mourning on Friday after gunmen killed the leading opposition figure, sparking fresh political turmoil, protests and a general strike which took Tunis to near standstill. AFP PHOTO / FETHI BELAID (Photo credit should read FETHI BELAID/AFP/Getty Images)
ምስል Fethi Belaid/AFP/Getty Images
Ali Larayedh
የቱኒዝያ ጠቅላይ ሚንስትር አሊ ላራዬድህምስል picture-alliance/AP
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ