1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አድማ እና ተቃዉሞዉ

ዓርብ፣ የካቲት 30 2010

የኦፌኮ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙላቱ ገመቹ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ የሚወገደዉ በኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ በዉጪ ኃይል አይደለም።

https://p.dw.com/p/2u3dd
Äthiopien Rex Tillerson und Moussa Faki Kommissionsvorsitzender Afrikanische Union (AU)
ምስል Getty Images/AFP/J. Ernst

የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቲለርሰን አዲስ አበባን በጎበኙበት ወቅት የተቃዋሚዉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባለሥልጣናትን እንዳላነጋገሩ የፓርቲዉ መሪዎች አስታወቁ።የኦፌኮ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙላቱ ገመቹ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ የሚወገደዉ በኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ በዉጪ ኃይል አይደለም።ካለፈዉ አርብ ጀምሮ በተደረገዉ አድማ እና ተቃዉሞ ሰበብ በሰዉ ሕይወት አካል እና ሐብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም አቶ ሙላቱ አስታዉቀዋል።አቶ ሙላቱን በስልክ አነጋግረናቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ