1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታሊባን ምክትል አዛዥ መያዝ

ማክሰኞ፣ የካቲት 9 2002

የፓኪስታንና የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅቶቸ በጋራ በወሰዱት የማጥቃት ዕርምጃ አንድ ከፍተኛ የታሊባን አመራር አባል በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ይፋ አደረጉ ።

https://p.dw.com/p/M3Bb
የታሊባን ጥቃት በአፍጋኒስታንምስል AP

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን የአፋጊስታን ታሊባኖች መሪ የሙላህ ኦማር ምክትል አብዱል ጋህኒ ባራዳር በደቡብ ፓኪስታንዋ የካራቺ ከተማ መያዛቸውን ዛሬ አረጋግጠዋል ። የታሊባኑ ምክትል አዛዥ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቀዋል ። የታሊባን ቃል አቀባይ ግን ባራዳር አፍጋኒስታን ውስጥ ናቸው ሲል አስተባብሏል ። የዶይቼቬለዋ Sabine Matthay የዘገበችውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ዛቢነ ማታይ/ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ