1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታሊባን ድልና አዉሮጶች

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 11 2013

ዩናይትድ ስቴትስ በመራችና ባዘዘችዉ ጦርነት በርካታ ወታደሮቻቸዉን ያሳተፉት የአዉሮጳ መንግስታት ጦሩ ከአፍቃኒስታን ለቅቆ እንዲወጣ የወሰኑትን የአሜሪካዉን ፕሬዝደት ጆ ባይደንን እየወቀሱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3z5vS
Weltspiegel 19.05.2021 | Deutschland Leipzig | Bundeswehr, Flug aus Afghanistan
ምስል Jens Schlueter/Getty Images

የዩናይትድ ስቴትስ ዉሳኔ፣ የታሊባን ድልና አዉሮጶች

 

ዩናይትድ ስቴትስ መራሹ ጦር ለ20 ዓመት ያክል የተዋጋዉ የአፍቃኒስታኑ የቀድሞ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ታሊባን ባልተጠበቀ ፍጥነትን ርዕሠ-ከተማ ካቡልን መቆጣጠሩ ዛሬም እያነጋገረ ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስ በመራችና ባዘዘችዉ ጦርነት በርካታ ወታደሮቻቸዉን ያሳተፉት የአዉሮጳ መንግስታት ጦሩ ከአፍቃኒስታን ለቅቆ እንዲወጣ የወሰኑትን የአሜሪካዉን ፕሬዝደት ጆ ባይደንን እየወቀሱ ነዉ።አንዳድ የአዉሮጳ ፖለቲከኞችና መሪዎች የአዉሮጳ ሕብረት በሕብረቱ የሚታዘዝና የሚመራ የመከላከያ ኃይል እንዲመሰርት እየጠየቁም ነዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ