1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የታሰረዉ የሃገሬ ታሪክ ይፈታ» ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

እሑድ፣ የካቲት 18 2010

«እንደምን አመሻችሁ ፤ እንኳን አደረሳችሁ ፤ ለፆሙ ብቻ አይደለም ፤ ለመፈታት ዜናም! ዛሬ አዳራሹ ሞልቶአል፤ ወንበር ሞልቶ መሬት ላይ የተቀመጡ ብዙ ሰዎች አያላሁ። ምንድነዉ እንዲህ የሞላበት ምክንያት ብዬ ስጠይቅ የተፈቱት መጥተዉ ነዉ አሉኝ» የዳንኤል ክብረት መነባንብ መግብያ

https://p.dw.com/p/2tEwl
Daniel Kibret
ምስል Privat

«አድዋ በጎሰኞች ዓይን»


ባለፈዉ ሰሞን  ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አድዋን በተመለከተ ባለፈዉ ሰሞን በአዲስ አበባ ራስ ትያትር ፖየቲክ ጃዝ ምሽት መድረክ ላይ  ያቀረበዉ የድምፅ ሥራ በማኅበራዊ መገናኛ ተለቆ በርካቶችን ሲያወያይ ፈገግ ሲያሰኝ ሰንብቶአል። ዲያቆን ዳንኤልን እስቲ ስለዚህ ስራህ እናዉራ አልነዉ እሺ አለ በሙሉ ልብ፤ ከዝግጅት ክፍላችን በባህላዊ በማኅበራዊ ብሎም በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ለትብብር ጥያቄ ሲቀርብለት ከመተባበር ወደኃላ ብሎ አያዉቅምና ዛሬም በማመስገን ቃለ ምልልሳችን ጀመርን። መጀመርያ ዲያቆን ዳንኤል ይህን ሥራህን አንተ ነህ ወይስ ሌሎች ናቸዉ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የለቀቁት? እዉቅናስ ሰተሃቸዉ ነበር? ስንል ጠይቀነዉ ነበር። በአዲስ አበባ ራስ ትያትር ያቀረበዉ ጽሑፍ ርዕስ «አድዋ በጎሰኞች ዓይን» ይሰኛል። ከዲያቆን ዳንኤል አዝናኝና እና ምክራዊ ቃለ ምልልስ ሰጥቶናል፤  ሙል መሰናዶዉን የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 
አዜብ ታደሰ