1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የታሰሩ ጋዜጠኞች ምርመራ

ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2011

አቶ ሔኖክ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት በደንበኞቻቸዉ ላይ የሚደረገዉ ምርመራ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር የማይገናኝ፣ እንዲያዉም ከሞያቸዉና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የተገናኘ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3MKtO
Äthiopien Addis Abeba Motorräder aus Stadt verbannt
ምስል DW/Solomon Musche

የታሰሩት ጋዜጠኞች ይዞታ

በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያና መዘዙ ተጠርጥረዉ የታሰሩ ጋዜጠኞች የእስር ቤት አያያዝ መሻሻሉን ጠበቃቸዉ አቶ አሔኖክ አክሊሉ አስታወቁ።ይሁንና አቶ ሔኖክ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት በደንበኞቻቸዉ ላይ የሚደረገዉ ምርመራ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር የማይገናኝ፣ እንዲያዉም ከሞያቸዉና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የተገናኘ ነዉ።አቶ ሔኖክ የሁለት ጋዜጠኞች ጠበቃ ናቸዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት «መፈንቅለ መንግስት» ከሚለዉ ግድያ በኋላ ያሰራቸዉን ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እንዲለቅ የመብት ተሟጋቾች እየጠየቁ ነዉ።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ