1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታደሰ እንግዳው ኅልፈትና ዶይቸ ቨለ፣

ሰኞ፣ ሐምሌ 9 2004

ጤናይስጥልኝ እንደምን አምሽታችኋል ? ዛሬ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳው ፣ አዲስ ዘገባ ሊያቀርብልን በዝግጅት ላይ ነበረ ፣ ግን አልሆነም! እጅግ ያሳዝናል! ከዚህ በኋላ ድምፁ በራዲዮ ሊሰማ አይቻልም ። ወጣቱ፤ ጎልማሳው ጋዜጠኛ ታደሰ

https://p.dw.com/p/15Yfj
ምስል DW

እንግዳው፤ ትናንት እሁድ፣ ከአዋሳ ወደ አዲስ አበባ ከ 2 ወንድሞቹ ጋር በመመለስ ላይ ሳለ፤ ከዜና ምንጮቻችን እንዳረጋገጥነው፣ ባጋጠመ የመኪና አደጋ ሳቢያ ፤ እርሱና፤ አንደኛው ወንድሙ ህይወታቸው አልፏል። በዚህ ዘግናኝ ህልፈተ ህይወት፣ ቤተሰብ ፤ ቤተዘመድ ፤ ጓደኞች ፣ እኛም የሥራ ባልደረቦቹ እጅግ አዝነናል። ስለሆነም የዛሬውን ሥርጭታችንን፣ ከሞላ ጎደል በአጠቃላይ፤ ለእርሱ መታሰቢያ እንዲሆን አድረገናል። በዚህ በራዲዮ ጣቢያው ማዕከል ከሚገኙ 6 ባልደረቦቹ ጋር የተካሄደው ልዩ ውይይት ፤ ቀጥሎ ይቀርባል።

ባልደረቦቹ