የቴሌ ኮሙኒኬሽን የሠራተኛ ማሕበር መታገድ
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 1 2003ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ የሠራተኛና አሠሪዎች ቦርድ ነባሩን የቴሌኩሙኒኬሽን የሠራተኛ ማሕበርን አገደነባሩ የቴሌ የሠራተኞች ማሕበር ኢትዮ-ቴሌ በሚል ሥም ባዲስ መልክ የተደራጀዉ መስሪያ ቤት ሠራተኞችን አላግባብ አባረረ፥ ደመወዝና ካሳ ከለከከለ፥ ኃላፊዎችን ከሙያና ከችሎታቸዉ ዉጪ መደበ በማለት መስሪያ ቤቱን ከሶ ሲከራከር ነበር። በክርክሩ መሐል ከሳሹን ማሕበር የሚቀናቀን ሌላ ማሕበር ተመስርቷል። አዲሱ ማሕበር ከተመሠረተ በሕዋላ የከሳሽ ተከሳሾች ክርክር ወደ ማሕበራት ሕጋዊ እዉቅና ተቀይሮ ነበር የሰነበተዉ። ዛሬ ግን የሠራተኛና አሰሪዎች ቦርድ ነባሩን ማሕበር ሽሮ ለአዲሱ ሕጋዊ እዉቅና ሠጥቷል።
ታደሰ እንግዳዉ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ