1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የትራምፕና የባይደን ክርክር

ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 2013

ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ከሁለት ሳምንት ግድም በኋላ በሚደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩት ሐገሪቱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የዴሞክራቱ ዕጩ ጆ ባይደን ዛሬ ሁለተኛና የመጨረሻ የቴሌቪዥን ክርክራቸዉን ያደርጋሉ።

https://p.dw.com/p/3kIt7
Donald Trump und Joe Biden
ምስል Patrick Semansky/AP Photo/picture-alliance

«የመጨረሻው ክርክር ዛሬ ይካሄዳል»

ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ከሁለት ሳምንት ግድም በኋላ በሚደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩት ሐገሪቱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የዴሞክራቱ ዕጩ ጆ ባይደን ዛሬ ሁለተኛና የመጨረሻ የቴሌቪዥን ክርክራቸዉን ያደርጋሉ። ናሽቪል-ቴኔሲ የሚደረገዉ ክርክር ከዚሕ ቀደም በተደረገዉ የክርክር ሒደት የታዩ የሥርዓት ችግሮችን ለማስወገድ ጥንቃቄና አዳዲስ ደንቦች ተደንግገዉበታል።በዘንድሮዉ ምርጫ ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያንን ጨምሮ በርካታ ሕዝብ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ነጋሽ መሐመድ አትላንታ ጆርጅያ የሚኖረዉን ጋዜጠኛ ታሪኩ ኃይሉን በስልክ አነጋግሮታል።
ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ