1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራምፕ አስተያየት እና ዉግዘቱ

ሐሙስ፣ ኅዳር 30 2008

በዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካኑ እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ ሙስሊሞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከመግባት እንዲታገዱ ካሉ በኋላ በአገሪቱ ስለ ጽንፈኛ አቋማቸዉ ዉይይትና ክርክሩ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ። በብሪታንያም ከ150 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ዶናልድ ትራምፕ ወደ ብሪታኒያ መግባት እንዲከለከሉ የተቃዉሞ ፊርማቸዉን አሰባስበዋል።

https://p.dw.com/p/1HLSL
US-Kandidat Trump fordert Einreise-Stopp für alle Muslime
ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካኑ እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕምስል picture-alliance/dpa

[No title]


በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ሰኞ እለት ነበር፤ የዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትረምፕ በማውንት ፕሌይዘንት ፣ ሳውዝ ካሮላይና የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከመግባት መታገድ አለባቸው ሲሉ የተናገሩት። ይህ የዶናልድ ትረምፕ ንግግር ህዝብ ጆሮ ከደረሰ በኋላ «ሲ ኤን ኤን» እና «ፎክስ»ን በመሳሰሉ ታዋቂ የብዙኃን መገናኛዎች እንዲሁም በትዊተርና በተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛዎች ትልቅ የመነጋገርያ ርዕስ ሆኖ ሰንብቷል። የዩኤስ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ፖሊስ ምክር ቤት ባልደረባ ላሪ ሃስ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣ዶናልድ ትረምፕን ጊዜ ጠብቀዉ የሚናገሩ አፈጮሌ ያሏቸው ሃስ በሙስሊሞች ላይ የተቃጣዉን የጥቃት ንግግራቸዉን አዉግዘዋል።

USA Präsidentschaftswahl Kanditat der Republikaner Donald Trump
ምስል AP / Montage DW


«ትራምፕ የአሜሪካን ፖለቲካን የሚያበላሽ ምስል ነዉ። ይህ ነገር በዩኤስ አሜሪካ በተወሰነ ጊዜ መልሶ የሚመጣ በተለይም በሪፐብሊካን ፓርቲ እዛም ብቻ ሳይሆን በሌላዉ ላይ የሚታይ ነዉ። ንግግሩ ራሱን ለማሳወቅ የዉጭ ዜጋ ጥላቻን ማስፋፋትን የሚያጠቃልል ነዉ። የዉጭ ዜጋዎች እንዲፈሩ ድንበሮች እንዲዘጉ የሚያነሳሳ ስሜትን ለመፍጠርም ነዉ። በአንዳንድ የፖለቲካ ንግግሮቹ የተወሰኑ አገር ህዝቦች ወይም ዝርያዎች ወደዚህ አገር አትምጡ አትግቡ የሚል መልክት ያዘለ ነዉ። እንዲህ አይነት ወደ አገር ዉስጥ የሚገቡ የዉጭ ዜጋዎችን የሚፃረር ጉዳይ ብዙ ጊዜ ገጥሞናል አይተናልም። »

Jeb Bush Vorwahlkampf Präsidentschaftswahlen
ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካኑ እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕምስል Getty Images/J. Sullivan

በዩኤስ አሜሪካ የቴሌቭዥን ስርጭቶች ዶናልድ ትረምፕን የሚደግፉ ተናጋሪዎች ይቀርባሉ። ስለንግግሩ አያጋበንም የሚሉም አልጠፉም። በርግጥ አጋጣሚ ይሁን አይሁን አይታወቅም እንጂ አብዛኞቹ ይህን አይነት አስተሳሰብ ያላቸዉ ላለመታወቅ ጥቁር የፀሐይ መነጽር ሲያደርጉም ይታያል። እንድያም ሆኖ ሃስ አብዛኞቹ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት፣ ሙስሊሞች ወደ ዩኤስ አሜሪካ እንዳይገቡ ማገድ በአገሪቱ ሊከሰት የሚችለዉን የአሸባሪ ጥቃት ይከላከላል በሚለዉ በትራምፕ ኃሳብ ይስማማሉ የሚል እምነት የላቸዉም።


«ይህ ሪፐብሊካኖች ስለ ፍልሰት ከሚከተሉት የአስተሳሰብ መንገዶች ጋር የሚያያዝ ነው ። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ሜክሲካውያንና የስጳኝ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ በደቡብ በኩል ድንበራችን ላይ ትልቅ ግንብ መገንባት ሲሉ ይሰማል። ይህ ደግሞ የዉጭ ጉዱይ መርሃቸው ሳይሆን የፍልሰት ፖለቲካ አቋማቸው ነዉ። »
የዶናልድ ትራምፕ አይነት ጊዜን ጠብቆ የሚነሳ የብልጣብልጥ አነጋገር በዩኤስ አሜሪካ ሲታይ የመጀመርያ እንዳልሆነ ላሪ ሃስ ይገልፃሉ። እንደ ሃስ በ 1930 ዓመታት አሜሪካዉያን በእንደዚህ ዓይነት ጊዜና ወቅትን ጠብቆ በሚቀርብ ጠብ አጫሪ ንግግር በሚጥል ግለሰብ አገሪቱ ከፍተኛ የኤኮኖሚ ቀዉስ ደርሶባታል። በዚያ ወቅት ፈርዘር ኮግልን የተባሉ አንድ የሃይማኖት አባት አንድ ሚሊዮን ሕዝብን ሰብስበዉ ለሁሉ ነገር ጥፋተኞቹና ተጠያቄዎቹ አይሁዶች ናቸዉ ሲሉ እንደነበር ነበር ሃስ አስታውሰዋል።
የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ብሎግ «የዶናልድ ትረምፕ የጥላቻ ማስፋፍያ ንግግር ሊደነቅ አይገባም» ሲል አስተያየቱን አስቀምጦአል። በዩኤስ አሜሪካ ምርጫ ዋንኛ በተባለዉ በሎዋ ግዛት በተደረገ የመጠይቅ መዘርዝር ሽንፈት ከደረሰባቸዉ ፖለቲከኞች ከሪፐብሊካኑ ፓርቲ አባል ከቴድ ክሩዝ ቀጥሎ ሁለተኛዉ ዶናልድ ትረምፕ መሆናቸዉ ተዘግቦአል። ይህ የዶናልድ ትረምፕ ጥላቻ አዘል አስተያየት ከተለያዩ የሃገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ፣ ከተቀናቃኛቸው ጄብ ቡሽ ጭምር ውግዘት ተፈራርቆበታል።

Nahost Berichterstattung Symbole
የትራምፕ ተቀናቃኝ ጄብ ቡሽምስል Reuters/J. Skipper

ጊሮ ሽሊስ / አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ