1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

    የትነበርሽ ተሸለመች

ማክሰኞ፣ መስከረም 16 2010

የትነበርሽ 371 ሺሕ ዶላር የሚያስገኘዉን የዘንድሮዉን ሽልማት ከሌሎች ሰወስት ተሸላሚዎች ማለት ከአዘርባጃንዋ ጋዜጠኛ፤ከሕንዳዊዉ ጠበቃ፤ እና ከአሜሪካዊዉ የሕግ ባለሙያ ጋር ይጋራሉ።ከዓለም ሕዝብ 15 በመቶዉ ወይም ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጠዉ አካል ጉዳተኛ ነዉ

https://p.dw.com/p/2kl1Q
Äthiopien Gewinnerin des alternativen Nobelpreises, Yetnebersh Nigussie
ምስል light for the world

«ሕይወት እንድንፈታት የተሰጠችን እንቆቅልሽ ናት» የትነበርሽ

«ሕይወት እንድንፈታት የተሰጠችን እንቆቅልሽ ናት» ትላለች ኢትዮጵያዊቷ የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋች የትነበርሽ ንጉሴ።እራስዋም አይነስዉር ናት።አካል ጉዳተኞች መብታቸዉ እንዲከበር፤ሕብረተሰቡ እንዲቀበል፤ እንዲንከባከባቸዉ የምትሟገት የ35 ዓመት የሕግ ባለሙያ ናት።የትነበርሽ ለአካል ጉዳተኞች መብት መከበር ላደረገችዉ አስተዋፅኦ አማራጭ ኖቤል ወይም ራይት ላይቭሊሁድ የተባለዉን ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸንፋለች።የትነበርሽ 371 ሺሕ ዶላር የሚያስገኘዉን የዘንድሮዉን ሽልማት ከሌሎች ሰወስት ተሸላሚዎች ማለት ከአዘርባጃንዋ ጋዜጠኛ፤ከሕንዳዊዉ ጠበቃ፤ እና ከአሜሪካዊዉ የሕግ ባለሙያ ጋር ይጋራሉ።ከዓለም ሕዝብ 15 በመቶዉ ወይም ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጠዉ አካል ጉዳተኛ ነዉ።የትነበርሽን በስልክ አነጋግሬያታለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ