1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትንሳኤ በአል አከባበር በጀርመናዉያን

እሑድ፣ መጋቢት 26 2002

እንኳን ለትንሳኤ በአል አደረሳችሁ ፣ጀርመናዉያን ደግሞ በቋንቋዋቸዉ Frohe Ostern ይሉታል፥ የደስታ ትንሳኤ ይሁንላችሁ ይሆናል ትርጉሙ። ባህላዊ መዝሙርም አላቸዉ፣ በሩቅ በቅርብም ያላችሁ የደስታ ትንሳኤ ይሁንላችሁ ይሰኛል። ጀርመናዉያን ትንሳኤን እንዴት ያከብሩታል?

https://p.dw.com/p/Mmir
ምስል picture-alliance/ dpa

ጀርመናዉያን የትንሳኤ በአልዘንድሮ ከኛ የፋሲካ ክብረ በአልጋር ገጥሞአል። እንደዉም በአንዳንድ የባህልድረ-ገጾቻቸዉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድሮ ከጀርመናዉያኑ ጋር በጋራ የትንሳኤን በአልበማክበር እንቁላልፍለጋ ይሄዳሉሲሉጽፈዋል። ጀርመናዉያን የትንሳኤ በአልን ሲዳረስ እንቁላልን በመቀቀልእና በመቀለም የትንሳኤን በአልስለምቀበሉት ነዉ። ታድያ ፋሲካ ሲዳረስ በየሱቁ የተቀቀለ እና በተለያዩ ቀለማት የተሸለመ እንቁላልበየመደቡ ተደርድሮ ይታያል። ወዳጅም ይህንኑ እንቁላልእንኳን ለትንሳኤዉ አደረሳችሁ ሲልያበረክታል። እዚህ ራድዮ ጣብያችን በገኘት በቦን ከተማ የሚኖሩ የዉስጥ ደዊ በሽታ ዶክተር ክላዉዲያ ቦንከ ጀርመናዉያን የትንሳኤን በአልበጣም እንወዳለን እናከብራለንም ሲሉይገልጻሉ
«የትንሳኤ በአልአከባበርን የምንጀምረዉ ከአርብ ከስቅለት ጀምረን ነዉ። የስቅለት እለት በፀጥታ በርጋት ስራ ሳንሄድ ቤታችን ሆነን የምናሳልፈዉ፣ ራሳችንን የምንጠይቅበት፣ ከሃጥያት ለመንጻት የምንጥርበት የን ነዉ። በአብዛኛዉ ጀርመናዉያ በዚህን እለት የሚመገቡትም ከአሳ የተሰራ የተለያዩ ምግቦችን ነዉ። ቅባት፣ ወተት፣ እንዲሁም እንቁላልአንበላም። ቅዳሜ ምሽት ላይ ቤተክርስትያን የቅዳሴ፣ የመዝሙር ስነ-ስርአት ስለሚኖር፣ በርካቶቻችን ወደ ቤተክርስትያን እንሄዳለን። በስቅለት ቀን ሁሉም ወደ ራሱ የሚመልስበት፣ እራሱን የሚጠይቅበት፣ ወደ ራሱ የሚመለስበት እለት ነዉ»
የፋሲካ በአልሲዳረስ በክረምት ብርድ እና ጭጋግየተሸነፈዉ የምዕራቡ አለም፣ ጭራሮ ሆነዉ ቆመዉ ይታዩ የነበሩት ዛፎች፣ ቅጠላቸዉ መለምለም የሚጀምርበት እንቡጥ አበባዎች ብቅ የሚሉበት፣ የሜዳዉም ሳር አረንጓዴ የሚሆንበት ወቅት ነዉ። በየቁጥቋጦዉ ስር ጉድጓድ ምሰዉ የሚኖሩት ጥንቸሎችም ከጉድጓዳቸዉ እየወጡ በየሜዳዉ ሲቦርቁ ሲሮጡ የሚታዩበት በመሆኑ ይመስላልበጀርመን እንዲሁም በሌሎች የኡሮጻ አገራት በጥንቸው ቅርስ ከረሜላ ቸኮላት፣ ሌላም ጣፋጭ ሰርተዉ በየሱቁ መሸጥ የሚጀምሩት ዶክተር ክላዉዲያ ቦንከም በመቀጠልሌላዉ ይላሉሌላዉ እንቁላልሞትና ህይወትን የምናሳይበት በምሳሌ የምናቀርበዉ ነዉ« ከቤተክርስትያን መልስ የቀለምነዉን የተቀቀለ እንቁላልበጓሮአችን ወይም በምንኖርበት ቤት ደብቀን በተለይ ህጻናትን ፈልጋችሁ አግኙ ብለን እቅንቁላሉን እንዳገኙ፣ ደግሞ ያገኝ ትንሽ ስጦታ እና የተቀለመዉን እንቁላልየሚያገኝበት ጣፋች እንደልቡ የሚያገኝበት ቀን ነዉ»
በጀርመን አገር ለፋሲካ ክብረ በአል ከአርብ ማለት ከስቅለት ጀምሮ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ይዘጋሉ። ይኸዉም ከአርብ የጀመረ እስከ ሰኞ ዝግሆኖ ሲዉል፣ ህዝቡ ወደ ስራዉ የሚመለሰዉ ማክሰኞ እለት ይሆናል። ታድያ ቅዳሜ እለት በየመንደሩ ያለዉ የምግብ አልያም የመጠጥ መሸጫ ሱቅ በህዝብ ስለሚጨናነቅ በብዛኛዉ ህዝቡ የፋሲካን ገበያ የሚያጠናቅቀዉ ሁለት ሳምንት ሲቀረዉ ጀምሮ ነዉ። የመጨረሻዉ የገበያ ቀን ከስቅለት በኻላ ያለዉ ቅዳሜ ሲሆን የዛን እለት ገበያ የሚሄደዉም ታድያ ጥቂት ህዝብ አይደለም። ዶክተር ክላዉዲያ ቦንከ በበኩላችዉ «ቅዳሜ ገበያ ዉለን ከስጋ የተሰራ የተለያዩ አይነት ወጦችን ሰርተን ወይም ጠብሰን ከቤተዘመድ ጋር የምንበላበት እለት ነዉ። በትንሳኤ እለት የምንጋግረዉ ዳቦ ወይም ጣፋጭ የጥንቸል ቅርጽ ያለዉ ነዉ»
ጥንቸል የጸደይ ወርን መግባት አዲስ ህይወትን፣ የአበቦችን ማበብ፣ አረንጓዴን መልበስ አመላካች አድርገን ነዉ የምንወስደዉ ሲሉ ይገልጻሉ፣ በመቀጠልም እሁድ ከሰአት በኻላ ከቤተሰቦቻችን ጋር በመሆን ሽርሽር እንወጣለን ታድያ የፋሲካ ሽርሽር አድርገናል እንላለን። ይህ በጀርመናዉያን ቤት የተለመደ ነዉ።
ጀርመናዉያን ከእሁድ የፋሲካን በአል አክብረዉ አመሻሽ ላይ ከቤተሰብ ጋርሽርሽር ወጥተዉ፣ በነጋታዉ ሰኞ እኛ ኢትዮጽያዉያን ማእዶት የምንለዉን እለት Ostermontag ይሉታል። ማእዶት በቋንቋዋችን መሸጋገርያ እንደምንለዉ ሁሉ ጀርመናዉያንም ማእዶትን ከጨለማ ወደ ብርሃን የተሸጋገርበት፣ ከሰይጣን ባርነት ነጻነት የሆንብት የተሸጋገርንበት ሲሉ ያከብሩታል። እንኳን ለትንሳኤዉ አደረሳችሁ!

Kind mit Osterhase
ምስል dpa

አዜብ ታደሰ