1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ መስተዳድር ሶስት ኩባንዮች አክሲዮን ሊሸጥ ነዉ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 2011

የኮሚኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀዉ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽንና ትራንስ ኢትዮጵያ የተባሉትን ኩባንዮች ድርሻ ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ አቅዷል

https://p.dw.com/p/3LrqB
Afrika Handel Inland LKW
ምስል picture-alliance/dpa/E. Strigl

የትግራይ ክልል ኩባንዮች አክሲዮን ሊሸጥ ነዉ

      
የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (በትግርኛ ምህፃሩ ትእምት) የሚያስተዳድራቸዉ ሶስት ኩባንዮች አክሲዮንን ለሽያጭ እንደሚያቀርብ የክልሉ መስተዳድር አስታወቀ።የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀዉ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽንና ትራንስ ኢትዮጵያ የተባሉትን ኩባንዮች ድርሻ ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ አቅዷል።የሶስቱን ኩባንዮች አክሲዮንን ዉጪ ሐገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዲገዙ ተጠይቀዋል።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ እንደሚለዉ በትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ትእምት) ኩባንዮች ላይ የክልሉ መስተዳድር የሚያደርገዉ ለዉጥ ድጋፍና ተቃዉሞ ገጥሞታል።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ